1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ያለመተማመን፤ የሰላም ውይይት እንቅፋት

እሑድ፣ መስከረም 15 2015

ሁለት ዓመት ሊደፍን ሳምንታት የቀረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተለይ በያዝነው ሳምንት መባባሱ እየተነገረ ነው። በትግራይ ክልል ውስጥም ሆነ በቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የሲቪክ ማኅበራት ጦርነቱ ቆሙ ተፋላሚ ኃይሎች ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል። የሰላም ድርድሩ ግን የተቀናቃኝ ወገኖች አለመተማመን ጋርዶታል።

https://p.dw.com/p/4HIQq
Äthiopien | Addis Abeba Olusegun Obasanjo

እንወያይ፦ ያለመተማመን፤ የሰላም ውይይት እንቅፋት

ሁለት ዓመት ሊደፍን በሳምንታት የሚቆጠር ዕድሜ የቀረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በተለይ በያዝነው ሳምንት መባባሱ እየተነገረ ነው። ጦርነቱ በአንድ ወገን ፣ በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት የሚደርስባቸው ወገኖች ሞትና መፈናቀል በሌላው ወገን የሚያንገላታው ማኅበረሰብ የኑሮ ውድነቱም ሌላ ጫና ሆኖበታል። አዲሱ ዓመት 2015 እንደው ቀኑና ወሩ ተለወጠ እንጂ ሀገሪቱ በአሮጌ ችግር እየዳከረች ነው። ሀገሪቱን ከጦርነት አዙሪት ያወጣል የተባለለት የሰላም ድርድር ለወራት ቢወራለትም ተግባራዊ እንዳይሆን በተፋላሚ ኃይሎች መካከል ያለው አለመተማመን እንቅፋት መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪቃው ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ይፋ አድርገዋል። ትግራይ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ከ70 በላይ ሲቪል ማሕበራት የህዝቡን ስቃይ ችላ ተብሏል በሚል ተፋላሚ ኃይሎችን ወቅሰው ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ ሲጠይቁ፤ ህወሃት በበኩሉ በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ተከፍቶብናል በሚል ለመላው ትግራይ የክተት ጥሪ አስተላልፏል። ያገረሸው ጦርነት፤ መፍትሄ የታጣለት መተማመን የጠፋበት ፖለቲካ እንዲሁም የሰላም ተስፋ ይኖር ይሆን በሚል ሦስት እንግዶችን ጋብዘን ውይይት አካሂደናል። ውይይቱን የድምጽ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ።

ሸዋዬ ለገሠ