ዩናይትድ ስቴትስ፤ ግድያና አፀፋ ግድያ
ዓርብ፣ ሐምሌ 1 2008ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ነጭ ፖሊሶች የሐገሪቱን ጥቁር ዜጎች በተደጋጋሚ መግደላቸዉ የጫረዉ ቁጣ፤ ተቃዉሞና አፀፋ እርምጃ የዓለም ልዕለ ሐያሊቱን ሐገር ግራ ቀኝ እያላጋት ነዉ።ነጭ ፖሊሶች ሰሞኑን ሁለት ጥቁሮችን መግደላቸዉ ያስቆጣቸዉ ታጣቂዎች ዳላስ ዉስጥ በፖሊስ ላይ በከፈቱት የበቀል ተኩስ አምስት ፖሊስ ገድለዉ ስድስት አቁስለዋል።በተለያዩ ከተሞች የሚኖረዉ ሕዝብ ደግሞ በየአደባባዩ በመሠለፍ የነጭ ዘረኛ ፖሊሶችን እርምጃ አዉግዟል።የሐገሪቱ ፖለቲከኞች እየተካረረ የመጣዉን ግጭትና ግድያ ለማቀዝቀዝ እየሞከሩ ነዉ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለስ