1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ተግዳሮቶች እና ተስፋዎች

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 24 2009

በ2017፣ ከሁለት ቀናት በፊት ከተሸኘው ከ2016 ችግሮች ምን ያህሉ ይቀረፋ ሉ ስንቱስ ይወረሳሉ ? አዲሱ ዓመትስ የሰላም ፣የመግባባት እና የብልጽግና ዓመት ወይንስ የአምባጓሮ የብጥብጥ እና የፍጥጫ ዓመት ይሆናል ?

https://p.dw.com/p/2V8Ug
Australien Sydney Jahreswechsel Feuerwerk
ምስል Reuters/J. Reed

  የ2017 ተግዳሮቶች እና ተስፋዎቹ 

ጎርጎሮሳዊው 2017 ዓም ከገባ ዛሬ ሁለተኛ ቀን ተቆጠረ ። ዘመኑን በጎርጎሮሳዊው ቀመር የሚያሰላው ዓለም ዓለም ባለፈው ዓመት የደረሱ ውድመቶች ሰቆቃዎች እና ስደት እንዳይደገም በመመኘት አዲሱን ዓመት ተቀብሏል ።ይሁንና በ2017፣ ከሁለት ቀናት በፊት ከተሸኘው ከ2016 ችግሮች ምን ያህሉ ይቀረፋ ሉ ስንቱስ ይወረሳሉ ? አዲሱ ዓመትስ የሰላም ፣የመግባባት እና የብልጽግና ዓመት ወይንስ የአምባጓሮ  የብጥብጥ እና የፍጥጫ ዓመት ይሆናል ? በዚህ ወቅት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች ናቸው ።  የዛሬው ማህደረ ዜና በ2017 የዓለም ተግዳሮቶች እና ተስፋዎቿ ላይ ያተኩራል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ አዘጋጅቶታል ።

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ