1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ ICC እና የአፍሪቃ መንግስታት ዉዝግብ

ዓርብ፣ ኅዳር 16 2009

እስካሁን ድረስ ብሩንዲ፤ ጋምቢያ እና ደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤቱ አፍሪቃዉያንን መጨቆኛ መሳሪያ ሆኗል በማለት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎችም ለመዉጣት እያስጠነቀቁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2TGjg
Niederlande Den Haag Internationaler Gerichtshof
ምስል picture-alliance/AP Images/J. Lampen

(Beri.Brüssel) ICC-Afrika - MP3-Stereo

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት (ICC) ከአፍሪቃ መንግስታት የሚሰነዘርበት ቅሬታና ወቀሳ እንደቀጠለ ነዉ። ዘ-ሔግ ኔዘርላንድስ የሚያስችለዉ ፍርድ ቤት ሥራዉን የጀመረዉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ2002 ነበር።የፍርድ ቤቱን መመሥረቻ ሰነድ 124 ሐገራት ቢፈርሙም በፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉስጥ ድምፅን በድምፅ የመሻር ሥልጣን ያላቸዉ ዩናይትድ ስቴትስ፤ ሩሲያና ቻይና ግን አልፈረሙም። እስካሁን ድረስ ብሩንዲ፤ ጋምቢያ እና ደቡብ አፍሪቃ ፍርድ ቤቱ አፍሪቃዉያንን መጨቆኛ መሳሪያ ሆኗል በማለት ከአባልነት ሲወጡ፤ ሌሎችም ለመዉጣት እያስጠነቀቁ ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ