1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታና የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ምላሽ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 29 2012

ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮችና የአባላት እስራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ ፈተና መደቀኑን አስታወቁ፡፡በቅርቡ በክልሉ በነበረው አለመረጋጋት 16 አባላቶቹ መገደላቸውን ኦፌኮ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3gOxn
Deutschland Äthiopiens Oromo federalist congress |  Merera Gudina
ምስል Eshete Bekele Tekele/DW

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረንስ ስሞታ እና የምርጫ ቦርድ ምላሽ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአመራሮችና የአባላት እስራት እንዲሁም በተለያዩ አከባቢዎች የጽህፈት ቤቶቻቸው መዘጋት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው ላይ ፈተና መደቀኑን አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በክልሉ በነበረው አለመረጋጋት 16 አባላቶቹ መገደላቸውን ኦፌኮ ገልጿል።የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቃለ አቀባይ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የፓርቲው አመራሮች መታሰራቸውን እና በሂደቱም ፓርቲው ጉዳዩን የመከታተል  መብት እስከማጣት መድረሱን አመልክተዋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሚዩንኬሽን አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር በኩል የቀረበላቸውን አቤቱታ ተመልክተው ለአዲስ አበባ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽኖች ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸው፤ በኦፌኮ በኩል እስካሁን የደረሰን ቅሬታ የለም ብለዋል፡፡

 Logo Oromo Liberation Front

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ