1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ንግግር

ዓርብ፣ ጳጉሜን 2 2004

ፕሬዝዳንቱ በዚሁ ምሽት ባሰሙት ንግግር የጀመሯቸውን በጎ ተግባራት ከግብ ያደርሱ ዘንድ ህዝቡ ዳግም እንዲመርጣቸው ጠይቀዋል ። ተቀናቃኛቸውን የሪፐብሊካኑን ዕጩ ሚት ሮምኒን የውጭ ፖሊሲ ልምድ የሌላቸው ሲሉ አጣጥለዋል ። ኦባማ ተጨማሪ የሥራ እድል ለመፍጠር ፣ የኮሌጅ ተማሪዎችን የእዳ ጫና ለመቀነስ ና ሠራተኞችን ለማሠልጠን ቃል ገብተዋል ።

https://p.dw.com/p/1651C
U.S. President Barack Obama waves as he arrives to address delegates during the final session of the Democratic National Convention in Charlotte, North Carolina, September 6, 2012. REUTERS/Jason Reed (UNITED STATES - Tags: POLITICS ELECTIONS) // Eingestellt von wa
ምስል reuters

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሐገራቸዉን የገጠመዉ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀትን ለማስወገድ ረጅም ጊዜ እንደሚጠይቅ አስታወቁ።ኦባማ የዲሞክራቲክ ፓርቲያቸዉን ወክለዉ ለድጋሚ ዘመነ-ሥልጣን እንደወዳደሩ የፓርቲዉ ጉባኤ ያሳለፈዉን ዉሳኔ መቀበላቸዉን ትናንት ሲያስታዉቁ እንዳሉት ለዘመናት የተጠራቀመዉ የሐገራቸዉ ችግር ባጭር ጊዜ አይወገድም።ያም ሆኖ ችግሩን ለማቃለል መስተዳድራቸዉ የወሰደዉ እርምጃ አበረታች ዉጤት ማሳያቱን አስታዉቀዋል።ኦባማ ዩናይትድ ስቴትስ በ1930ዎቹ ሥልጣን ላይ በነበሩት በፕሬዝዳት ሩዘቬሌት ዘመን ከታየዉ ኪሳራ ወዲሕ ለመጀመሪያ ጊዜ የገጠማትን ያሉትን ኪሳራ ለማስወገድ በመጀመሩት ጎዳና መቀጠሉ አስፈላጊ ነዉ።

«የቀየስኩትን መንገድ ፈጣንና ቀላል ለማስመሠል አልፈልግም። ይሕን አድርጌዉ አላዉቅምም። የመረጣችሁኝ ለመስማት የምትፈልጉትን እንድነግራችሁ አይደለም።እዉነቱን እንድነግራችሁ እንጂ።እዉነቱ ደግሞ ለብዙ አስርታት የተጠራቀሙትን ፈተናዎች ለማለፍ ከጥቂት አመታት በላይ ጊዜ ይጠይቃል።ኪሳራዉን ለማቃለል፥ አሁን ከገጠመን የከፋዉን ብቸኛ ድቀት ለማስወገድ ፕሬዝዳት ሩዘቬልት እንዳደረጉት አይነት የጋራ ጥረት፥ የጋራ ሐላፊነት፥ ጠንካራና ያልሠለሠ እርምጃ ያሻል።»

ኦባማ ለድጋሚ ዘመነ-ሥልጣን ከተመረጡ የሥራ አጡን ቁጥር፥ የ,መንግሥታቸዉንና ወጪና ግብር ለመቀነስ ቃል ገብተዋል።ፕሬዝዳት ኦባማ ትናንት ያደረጉት ንግግር ከአራት ዓመት በፊት እንዳደረጉት ያድማጭ ስሜትን የሚፈነቅል አይነት ግን አልነበረም።ኦባማ በመጪዉ ጥቅምት አጋማሽ ለሚደረገዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከሪፐብሊካኑ ተቀናቃኛቸዉ ከሚት ሮምኒ ጋር ይፎካከራሉ።

ነጋሽ መሐመድ

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ