1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፕረስ ነጻነት፤ኢትዮጵያና ኤርትራ

ሐሙስ፣ ጥር 23 2005

ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባው ምስራቅ አፍሪቃ ከሶሪያ ቀጥሎ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉ የሚጣስበት አከባቢ ሆኗል። ኤርትራ ለስድስተኛ ጊዜ በመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጥላች።

https://p.dw.com/p/17Vor
A protester holds a placard reading 'Secret State, don't let the info bill see the light of day" during a anti secrets bill protest at parliament in the city of Cape Town, South Africa, Tuesday, Nov 22, 2011. South African lawmakers have approved a committee report recommending passage of a bill to protect state secrets. The bill is expected to be passed later Tuesday, though critics say it will stifle expression. Retired Archbishop Desmond Tutu and prominent writers led by Nobel laureate Nadine Gordimer have lobbied against the bill. (Foto:Schalk van Zuydam/AP/dapd)
ምስል dapd

ፈረንሳይ ፓሪስ የሚገኘው ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ትናንት ባወጣው የፕሬስ ይዞታ ዘገባው፤ ኢትዮጵያን ከ179 ሀገራት 137ኛ ደረጃ ላይ ሲያስቀምጥ ኤርትራ ደግሞ በመጨረሻ ላይ ትገኛለች። እንደ ዘገባው በኤርትራ የመገኛኛ ብዙሃን ነጻነትና የጋዜጠኞች አያያዝ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ሀገሪቷ ያለ ጋዜጠኞች ልትቀር ትችላለች። ኢትዮጵያ ውስጥ የጋዜጠኞች መታሰርና የፀረ ሽብር ህግ የፕሬስ ነጻነትን እያዳከመ ነው። የድርጅቱ የአፍሪቃ ክፍል ተጠሪ ፕየር ኦምብሯዝን ፕየር ን ያነጋገረው ገመቹ በቀለ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ትናንት ይፋ ባደረገው ዘገባው ምስራቅ አፍሪቃ ከሶሪያ ቀጥሎ የፕሬስ ነጻነት በእጅጉ የሚጣስበት አከባቢ ሆኗል። ኤርትራ ለስድስተኛ ጊዜ በመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጥላች። ይህም የሆነው በሁለት ምክንያቶች ነው ይላሉ በድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ቡድን የአፍሪቃ ክፍል ኃላፊ ኦምብሯዝን ፕየር

«አንደኛ፣ ምንም ዓይነት የግል ፕሬስ የለም። በሀገሪቱ የሚገኘው ብቸኛ የህዝብ መገናኛ በማስታወቂያ ሚኒስቴር፤ ማለትም በመንግስት የተያዘ ነው። ሁለተኛ፣ ኤርትራ ለጋዜጠኞች ትልቁ እስር ቤት ናት። ቢያንስ 30 ጋዜጠኞች በወህኒ ቤት ይገኛሉ።»


ድንበር የለሽ ጋዜጠኞች ከዳሰሳቸው 179 ሀገራት ኢትዮጵያ 137ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ኦምብሯዝ ፕየር እንዳሉት በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት አያያዝ አሳሳቢ ነው፣

«ኢትዮጵያን በተመለከተ ሁኔታው በርግጥ ትንሽ የተሻለ ቢሆንም አሁንም አሳሳቢ ነው፤ ምክንያቱም ጋዜጠኞች አሁንም በእስር ይገኛሉ፣ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ በሀገሪቱ ውስጥ የመረጃ ነጻነትን ለመገደብ ጥቅም ላይ ይውላል።»

ኤርትራ እአአ አቆጣጠር ከ2001 ጀምራ የጋዜጠኞችና ደህነትና እና የግል የመገናኛ ብዙሃን ነጻነት የሚያሰጋ እርምጃ ወስዳለች። በርካታ ጋዜጠኞች ሳይፈረድባቸው ከ10 ዓመት በላይ በእስር ቤት ቆይተዋል። ከነሱም ሰባቱ በደረሰባቸው የቁም ስቅል ምክንያት ሞተዋል ወይም ህይወታቸውን አጥፈተዋል። በእስር ቤት የቀሩት ጋዜጠኞች ህይወትም አሳሳቢ ነው፣

«ይህ ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ እርግጠኛ ነኝ የተቀሩ ጋዜጠኞች በእስር ይሞታሉ። በዚህ ሀገር ያለው ሰዎችን በእስር ቤት እንዲሞቱ የሚያደርግ ጨካኝ አምባገነን ነው። የሚሳስበኝ ነገር ቢኖር፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ በኤርትራ የሚቀሩ ጋዜጠኞ አይኖሩም፤ ምክንያቱም በእስር ቤት የሌሉ ሀገሪቷን በህገወጥ መንገድ እየለቀቁ፣ ከዚህ አምባገነን አገዛዝ ለማምለጥ ድንበር አቋርጠው እየሄዱ ነው»

ኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በመገናኛ ብዙሃን አፈና በተደጋጋሚ ስሟ ቢነሳም አሁንም ከምዕራብ መንግስታት ትልቅ ድጋፍ ይደረግላታል። ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች ቡድን ድጋፉ እንዲቀር ባይፈልግም በኢትዮጵያ ያለው የሰብዓዊ መብት አያያዝ በምዕራብ ሀገራት ተገቢ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ይላሉ ፕየር፣

«ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ እንዲያቋርጥ አንሻም። ኢትዮጵያ ከአፍሪቃ በጣም አስፈላጊ ሀገር ናት። በብዙ መልክ የምዕራብውያን ጠንካራ አጋር ናት። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲህ ዓይነቷን አስፈላጊ ሀገርና እገዛ የሚፈልግ ህዝብ መደገፍ እንደሚሻ አንረዳለን። የድርጅታችን ሚና የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሳይታይ፣ ይህ ድጋፍ ሊሰጥ እንደማይችል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለአውሮፓ ህብረት መናገር ነው።

Aerial view of Addis Ababa © derejeb #42996737
አዲስ አበባምስል derejeb/Fotolia
Straßenszene in der Independence Avenue in Asmara, der Hauptstadt von Eritrea, aufgenommen 1997.
አሥመራምስል picture-alliance/ dpa

ገመቹ በቀለ

ሒሩት መለሰ