1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፓኪስታን ጦርነትና የኑክሌር ቦምቧ ሥጋቱ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 28 2001

አዉዳሚዉ ቦምብ ከታሊባን ወይም ከአል-ቃኢዳ እጅ ይገባል የሚለዉን ሥጋት ግን የፓኪስታን መንግሥት አይቀበለዉም።

https://p.dw.com/p/Hkun
የታሊባን ደጋፊዎችምስል AP

በፓኪስታን ጦርና በታሊባን ደፈጣ ተዋጊዎች መካካል የሚደረገዉ ዉጊያ ማየል የፓኪስታንን የኑክሌር ቦምብ ከአክራሪዎቹ ሐይላት እጅ ይዶለዋል የሚል ሥጋት አስከትሏል።የፓኪስታን መንግሥት ጦር በደፈጣ ተዋጊዎቹ ላይ መጠነ-ሠፊ ጥቃት ቢከፍትም እስካሁን አስተማማኝ ድል አላገኘም።አዉዳሚዉ ቦምብ ከታሊባን ወይም ከአል-ቃኢዳ እጅ ይገባል የሚለዉን ሥጋት ግን የፓኪስታን መንግሥት አይቀበለዉም።ዋሽንግተን ዉስጥ ዛሬ ከፓኪስታንና ከአፍቃኒስታን አቻዎቻቸዉ ጋር የሚነጋገሩት የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳት ባራክ ኦባማም ይሕንኑ ጉዳይ ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።ይልማ ሐይለ-ሚካኤል ከርሊን ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

Yilma Hinz

Negash Mohammed

►◄