1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የመግባቢያ ሰነድ ሥምምነት

ማክሰኞ፣ ጥር 21 2011

ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማር በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ ሥምምነቱን የፈረሙት በከሠሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የኩባንያዉ ኃላፊ ቶማስ ሼፈርና የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አበባ አበበያሁ ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/3CN7U
Steinmeier Äthiopien VW
ምስል DW/L. Schadomsky

(Beri.AA) VW-EIC signe memorandum of understanding - MP3-Stereo

የጀርመኑ ግዙፍ አዉቶሞቢል  አምራች ኩባንያ  ፎልክስ ቫገን (VW-በጀርመንኛ ምሕፃሩ) ኢትዮጵያ ዉስጥ የመኪና መገጣጠሚያና መለዋወጪያን ጨምሮ  የመኪና ቁሳቁሶች ማምረቻና መሸጫ ማዕከላትን መክፈት የሚያስችለዉን የመግባባያ ሰነድ ከኢትዮጵያ የኢንቨስትመት ኮሚሽን ጋር ተፈራረመ።ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማር በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ላይ፣ ሥምምነቱን የፈረሙት በከሠሐራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የኩባንያዉ ኃላፊ ቶማስ ሼፈርና የኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አበባ አበበያሁ ናቸዉ።ግዙፉ የአዉቶሞቢል አምራች ኩባንያ በስምምነቱ መሠረት ኢትዮጵያ ዉስጥ መወረት ሲጀምር ለኢትዮጵያዉያን የሥራ ዕድል ይፈጥራል፣ ለሐገሪቱ የዉጪ ገበያ ዕድል ይከፍታልም ተብሏል።

ጌታቸዉ ተድላ የኃይለጊዮርጊስ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ