1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍቅር ፏፏቴ

እሑድ፣ ጥር 9 2002

የባህል መድረካችን በኢትዮጽያ የክላሲክ ሙዚቃ ማለት በረቂቁ ሙዚቃ ዙርያ ስር ያቆየናል። በኢትዮጽያ ወላጅ ለሌላቸዉ ህጻናት መርጃ እንዲዉል ታዋቂዉ የሙዚቃ አዋቂ ኢትዮጽያዊ አንድ የሙዚቃ አልበም አሳትሞ በገና በአል ሰሞን ለህጻናቱ አበርክቶአል።

https://p.dw.com/p/LY2I
ምስል AP

ካሳሁን አድማሱ ይባላል በሙዚቃ ስራዉ ከታዋቂ ኢትዮጽያዉያን ሙዞቀኞች ማለት ከአስቴር አወቀ ከአበበች ደራራ፣ ከአብይ ሰለሞን ከሻንበል በላይነህ ከዝናሽ ነጓስ ጋር ሙዚቃ በመቀመር አብሮ ሰርቶአል። መኖርያዉን በኢንግሊዝ አገር ያደረገዉ ሙዚቀኛ ካሳሁን አድማሱ የሙዚቃ ዝንባሌ ከልጅነቱ ጀምሮ እንደነበረዉ እና በአገር ቤት የሙዚቃ ትምህርቱን እንደጀመረ ይገልጻል።
ሙዚቀኛ ካሳሁን አድማሱ የአገራችን ባህላዊ የሙዚቃ መሳርያ በመጫወቱ ታዋቂ ሲሆን በአገር ቤት የጀመረዉን የዘመናዊ የሙዚቃ መሳርያ ትምህርት በኢንጊሊዝ አገር በመቀጠል በሙዚቃ ትምህርት በማስተር ደረጃ አጠናቅዋል። በክላሲክ ሙዚቃ ማለት በረቂቅ ሙዚቃ በመቀመሩ ታዋቂ የሆነዉ ካሳሁን 1998 አ.ም ዘመዴ የሚል ርእስ 1992 አ.ም አዲስ ትዉልድ በ 2000 አ.ም ልጅነቴ የሚል ርስእና አሁን በቅርቡ ደግሞ የፍቅር ፍፍቴ በሚል የክላሲክ ሙዚቃ አልበሙን በሙዚቃ አፍቃሪዎች ጆር እንዲደርስ አድርጓል። አሁን በቅርቡ የፍቅር ፍፍቴ በተሰኘ ያወጣዉ የረቂቅ ሙዚቃ አልብም ለየት የሚያደርገዉ በኢትዮጽያ ወላጆቻቸዉን ላጡ ህጻናት መርጃ እንዲዉል ያበረከተዉ በመሆኑ ነዉ።
የገና ስጦታ ለሰራዊት ጌታ ይባላል በአገራችን በባህላችን፣ ሙዚቀኛ ካሳሁን በገና ሰሞን ለሙዚቃ አፍቃሪዎች ጆሮ ያደረሳት የክላሲክ ሙዚቃ አልብምም፣ በኢትዮጽያ ወላጆቻቸዉን ላጡ የጎዳና ተዳዳሪ ህጻናት መርጃ እንዲዉል አንሆ ተብሎ ለሚጠራዉ የህጻናት መርጃ ድርጅት አስረክቦአል። ካሳ አድማሱ በዚህ በአዉሮጻ በሚካሄደዉ አለማቀፍ ኮንሰርት በተለይ ደግሞ የተባበሩት መንግስታት በሚያዘጋጀዉ በስደተኞች ድምጽ መታሰብያ ዝግጅት ላይ ይህንኑ የኢትዮጽያ ባህልን የተላበሰዉን የረቂቅ ሙዚቃ አዳዲስ ፈጠራዎችን በመጨመር ያወጣዉ የፍቅር ፍፍቴ Fountain of Love የሙዚቃ አልብም ለዉጭዉ አለም ባህልን ከማስተዋወቁ አልፎ፣ በአዲስ የሙዚቃ ቅኝት ወገንን ባለዉ ሞያ ለመርዳት መነሳቱ ይበል የሚያሰኝ እና ሊበረታታ የሚገባዉ ይመስለናል። እዚህ ላይ በዉጭዉ አለም ያለን ኢትዮጽያዉያን ባለን ሞያ ወገን የመርዳቱ ባህላችንን መዘንጋት የለብንም እላለሁ። መሰናዶዉን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ