1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፍርድ ሂደት እና ፀረ ሽብሩ ህግ፣

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2005

ዛሬ ችሎት የተቀመጠው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፣ ከ 3 ዓመት ገደማ በወጣው ፀረ አሸባሪነት አዋጅ የተከሰሱት 29 የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ፣ ጉዳያቸው ለታህሳስ 8 እንዲታይ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የአገሪቱ ህገ-መንግሥት ስለዜጎች

https://p.dw.com/p/16x1g
ምስል AP

መብት ያሠፈረውንና የፀረ አሸባሪነቱ አዋጅ እንዴት ይሆን የሚታየው፣ ተክሌ የኋላ የተካሳሾቹን ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጋን ና የ AI ን ተጠሪ በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ካለፈው ዓመት ጥር ወር ገደማ አንስቶ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ፤ መንግሥት በሃይማኖታችን ጉዳይ ጣልቃ አይግባብን በማለት በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞአቸውን ሲያሰሙ መክረማቸው የሚታወስ ነው። ባለፈው ሐምሌ ወር 29 የሙስሊሙ ማኅበረሰብ መሪዎች ተይዘው መታሠራቸው IPS የተሰኘው የዜና አገልግሎት ድርጅት እንዳለው፤ አዋጁ፣ ሰላማዊ ተቃውሞን የብሶት መግለጫን አሸባሪነት ነው ብሎ የሚተረጉም ነው። በመገናኛ ብዙኀን የሚቀርብ የሰላ ዘገባም ሆነ ሒስም አሸባባሪነትን የሚያደፋፍር ተደርጎ ነው የሚወሰደው። የ 29 ኙን ደንበኞቻቸውን ጉዳይ ለመከታተል ፍርድ ቤት ተገኝተው የነበሩት ጠበቃ አቶ ተማም አባቡልጋ --

በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ሳቢያ፣ ሰብአዊ መብት እንከን የሚያጋጥምበት ሁኔታ፣ከጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ አስተዳደር ወዲህ በአዲሱ መንግሥት ተሻሽሎ ይሆን? የ A I ትዝብት ምንድን ነው?የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት AI የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ ተማራማሪ Claire Beston—

«29 የሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላትና መሪዎች ፀረ አሸባሪነት በተሰኘው አዋጅ ተከሰዋል። ይህ የሆነው ደግሞ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ጠ/ሚንስትር ከሆኑ ወዲህ ነው። እናም የቆየው ጥብቅ ክትትል የሚደረግበት፣ የሰዎችን የተለያዬ አስተያየት በመንግሥት ላይ የመሰንዘር መብት የማረቁ እርምጃ እንደቀጠለ ነው። ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ትችትን ለማረቅ እርምጃ መውሰድ መቀጠሉ እንደማይቀር ጠቋሚ ነው። »

ክሌር ቤስተን፤ የፀረ ሽብርተኝነቱ አዋጅ ህገ-መንግሥቱን የሚጻረር ነው ይላሉ።

Gericht Gesetz Jura Hammer Waage
ምስል fotolia/junial enterprises

«የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ሐሳብን በነጻ መግለጽ ለሚቻልበት መብት ዋስትና ይሰጣል። የማህበራትን ነጻነትንም እንዲሁ። በሰላማዊ መንግድ ተቃውሞን ስለማቅረብም፣ በሚገባ ያብራራል። ፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ግን እንዚህን መብቶች ይጋፋል። የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ ሰፊና በግልጽ የተቀመጠ ባለመሆኑ የአዋጁን ህግ እንደፈለጉት በመተርጎም ህጋዊዊ መብትን ለምሳሌ ያህል ሐሳብን በነጻ መግለጽ፤ ጋዜጠኞች በሚያቀርቧቸው ዘገባዎች ሰዎች ጎዳና ላይ ወጥተው በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማቅረባቸውን ሽብርተኝነት ተብሎ ሊተረጎም ይችላል ማለት ነው። የፀረ ሽብረተኝነት አዋጁ በእነዚህ መብቶች ላይ ገደብ ስለሚያደርግ በእርግጥ ህገ-መንግሥቱንና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰብአዊ መብትን የመጠበቅ ግዴታዋን ይጻረራል።»

አቶ ተማም አባቡልጋ፣እንደሚሉት፤ ደንበኞቻቸው፤ እንኳንስ በአሸባሪነት የሚያስጠይቅ እርምጃ ሊወስድባቸው ቀርቶ ከመንግሥት ጋር እየተገናኙ ይወያዩ የነበሩ ሰዎች ናቸው። ከ 3 ዓመት ገደማ በፊት የወጣው ጽረ-ሽብሩ አዋጅ ህገ-መንግሥቱን ይጻረራል የሚለውን ሐሳብም እንደ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተጠሪዋን (ክሌር ቤስተን)ን ሐሳብ አቶ ተማምም ይጋራሉ--።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ