1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የፋሲካ ልዩ ዝግጅት

እሑድ፣ ሚያዝያ 20 2011

የዛሬዉ የበዓል ልዩ ዝግችታን አብዛኛ ክፍል የተለያዩ የኢትዮጵያን አካባቢዎችን በሚያብጠዉ ጎሳ ለበስ ጠብ፣ ግጭት፤ዉዝግብ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናለቁትን እናስብበታል።በዓለተኛዉ ክርስቲያንስ እኒያ ወገኖቹን ምን ያሕል ይዘክር ይሆን? አራት ዘጋቢዎቻችን የተለያዩ አካባቢዎችን ቃኝተዋል።የቅኝት ዉጤት ዘገባቸዉን በየተራ እናሰማችኋለን

https://p.dw.com/p/3Ha8M
Äthiopien Feierlichkeit l Ostern
ምስል DW/S. Muchie

ፋሲካ፣ ሸመታና ስራ

                                  

የሐዲድ መስመር ወጣቶች የተናጋሪዉ ንግግር አልጥም ሲላቸዉ «ጭንቅ ወይም ሒራር አታዉራ» የሚል አባባል ነበራቸዉ።ጋዜጠኞች ደግሞ «ማንኛዉም ዜና ጥሩ ዜና አይደለም» ይሉናል።በበዓሉ ጭንቅ ላለማዉራት እንፈልጋለን።እንጠነቃቀለንም።ግን ጭንቁ ካለ የሚወገድበትን ብልሐት መሻት እንጂ ተወራ-አልተወራ የሚያመጣዉ ለዉጥ የለም።ደግሞ የሆነና የሚሆነዉን መደበቅ ወይም አለማዉራትም ከመዋሸት ይከፋል።

እንዲሕ ሆኖ- የዛሬዉ የበዓል ልዩ ዝግችታን አብዛኛ ክፍል የተለያዩ የኢትዮጵያን አካባቢዎችን በሚያብጠዉ ጎሳ ለበስ ጠብ፣ ግጭት፤ዉዝግብ ከቤት ንብረታቸዉ የተፈናለቁትን እናስብበታል።በዓለተኛዉ ክርስቲያንስ እኒያ ወገኖቹን ምን ያሕል ይዘክር ይሆን? አራት ዘጋቢዎቻችን የተለያዩ አካባቢዎችን ቃኝተዋል።የቅኝት ዉጤት ዘገባቸዉን በየተራ እናሰማችኋለን።

ከአዲስ አበባ፣ ዩናንስ ገብረ እግዚአብሔር በዓል፣ገበያና ሥራን የዳሰሰበትን ዘገባ በበጓ ተማፅኖ ያሳርጋል።«መግደል ሽንፈት ነዉ» አለች በጓ ነዉ-የሚለዉ እሱ።እንስማዉ።

   

ዮሐንስ የአዲስ አበባን መሐል፤መሐልን ሲል፣ ሌላዉ ወኪላችን ሰለሞን ሙጪ ወደ ርዕሰ-ከተማይቱ ዳርቻ ዘልቆ ነበር ዛሬ።ለገ ጣፎ፣ ለገዳዲ።የሁለቱ አካባቢዎች ሥም የኢትዮጵጵያ መገናኛ ዘዴዎች የዉሎ-አምሽቶ ርዕሠ ከሆነ ሰወስት ወር ሆነዉ።ዛሬም አነሳነዉ።የኦሮሚያ መስተዳድር በሁለቱ አካባቢዎች የተሰሩ መኖሪያ ቤቶችን «ሕገ ወጥ» ብሎ ካፈራረሳቸዉ ወዲሕ «ባለቤት» የነበሩት የካባቢዉ ነዋሪዎች ተፈናቃይ ሆነዋል።ባፍታ በቃ ቤት አልባ።ሰወስት ወራቸዉ።የዛሬዉን በዓል በርግጥ ጦም አልዋሉም።ግን አንዷ እናት «ሁሉም የሚያምረዉ» በቤት ነዉ-ይላሉ እያነቡ።ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት ከመፈናቀላቸዉ በላይ ያሳዘናቸዉ መንግስት «የትናችሁ» እንኳን አለማለቱ ነዉ።ዝርዝሩን ሰለሞን ይንገረን።

Äthiopien Migration l Vertreibene in Tigray
ምስል DW/M. Hailesellassie

                                 

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል  ነዋሪ ክርስቲያኖች ከዓምናዉ ዘንድሮ በስንት ጣሙ ይላሉ።ዘንድሮ እንዳምናዉ «ጭንቅ» የለም።በመስተዳድሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሐገረ ስብከት ኃላፊዎችና ቀሳዉስት እንደሚሉት በግጭት ዉዝግብ የጋዩ ወይም የተጎዱ አብያተ ክርስቲያን አብዛኞቹ ተጠግነዋል፣ ሌሎቹ ዳግም እየታነፁ ነዉ።ጥቃት ፈርተዉ ከየከአካባቢዉ ሸሽተዉ የነበሩ ምዕመናንም ወደየቀያቸዉ ተመልሰዋል።የሶማሌ ክልል የኃይማኖት መሪዎች ልክ እንደ ለገጣፎ-ለገ ዳዲ ተፈናቃዮች ሁሉ መንግስትን ይወቅሳሉ። ስቅለትን ጅጅጋ ያሳለፈዉ የድሬዳዋ ወኪላችን መሳይ ተክሎ ተከታዩን ዘገባ ይዞ ዛሬ ለፋሲካዉ ድሬዳዋ ተመልሷል።

                                  

ከምስራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ፣ ወደ ሰሜን ስናልፍ የትግራይ ተፈናቃዮችን ችግር፣ በመንግሥት ላይ የሚሰነዝሩትን ቅሬታና ወቀሳ እንሰማለን።የትግራይ መስተዳድር እንደሚለዉ ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተፈናቃሉ አንድ መቶ ሺሕ የትግራይ ተወላጆች በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ሠፍረዋል።ወይም ተጠልለዋል።የመቀሌዉ ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ ተፈናቃዮቹ ከሰፈሩባቸዉ አካባቢዎች አካባቢዎችን አንዱን ጎብኝቶ ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሰለሞን ሙጬ

መሳይ ተክሉ

ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ

ነጋሽ መሐመድ

                                  

 

                              

 

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ