1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኩዌት ፕሬዝዳንት ዱቴርቴን ለጉብኝት ጋብዛለች

ረቡዕ፣ የካቲት 14 2010

ፊሊፒንስ በኩዌት አንዲት ዜጋዋ ተገድላ መገኘቷን ተከትሎ ወደዚያች የሚደረግ የስራ ስምሪትን አግዳለች። ዜጎቿንም ከኩዌት እያስወጣች ትገኛለች። የተፈጠረውን የዲፕሎማሲ ውዝግብ ለማርገብ እየሞከረች ያለችው ኩዌት የፊሊፒንሱ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ በሀገሯ ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ባለፈው ሰኞ ጋብዛቸዋለች፡፡

https://p.dw.com/p/2t6Yf
Philippinen v
ምስል Getty Images/AFP/M. Dejeto

ኩዌት ፕሬዝዳንት ዱቴርቴን ለጉብኝት ጋብዛለች

በኩዌት በቤት ሰራተኝነት ታገለግል የነበረች የአንዲት ፊሊፒናዊት አስክሬን በመኖሪያ ህንጻ ውስጥ ባለ ማቀዝቀዣ ውስጥ ከተገኘ በኋላ በፊሊፕንስ ከፍተኛ ቁጣ መቀስቀሱ አይዘነጋም፡፡ ዜናው ከተሰማ በኋላ ሞገደኛው የፊሊፒንሱ ፕሬዝዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ወደ ኩዌት የሚደረግ የስራ ስምሪትን አግደዋል፡፡

ዱቴርቴ በኩዌት ለሚሰሩ ዜጎቻቸው ሀገሪቱን ለቅቀው እንዲወጡ ነጻ የአየር መጓጓዣ ጭምር አዘጋጅተውላቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት የተፈጠረውን የዲፕሎማሲ ውዝግብ ለማርገብ እየሞከረች ያለችው ኩዌት ዱቴርቴ በሀገሯ ይፋዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ባለፈው ሰኞ ጋብዛቸዋለች፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተቀሰቀሰውን ውጥረት በተመለከተ በጅዳው ዘጋቢያችን ነቢዩ ሲራክ የተጠናቀረውን ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።

ነቢዩ ሲራክ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ