1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያናት ፀሎትና ጾም

Negash Mohammedረቡዕ፣ ሐምሌ 20 2008

ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ ይፀልዩ በነበሩ ሽማግሌ ቄስ ላይ የተፈፀመዉ ግድያ፤ ቤተ-እምነቶች ቅዱስ በመሆናቸዉ የተጠለሉባቸዉ ሁሉ ክፉ እንዳይደርስባቸዉ የሚከለክለዉን ነባር ስምምነት የጣሰ እርምጃ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1JWmD
Frankreich Hollande mit Vertretern der Religionen
ምስል Getty Images/AFP/B. Guay

[No title]

ሰሜናዊ ፈረንሳይ የሚገኝ አንድ ቤተ-ክርስቲያን ዉስጥ የገቡ ሁለት ግለሰቦች አንድ አዛዉንት ቄስ መግደላቸዉ አስደንጋጭ ክስተት ነዉ የሆነዉ።በመላዉ ዓለም የሚገኙ የካቶሊክ ክርስትና እምነት ተከታዮች ዛሬ ሟቹን ቄስ አስበዉ ዉለዋል።እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) አባላት ናቸዉ ተብለዉ የተጠረጠሩት የቄሱ ገዳዮች ወዲያዉ ተገድለዋል። የዶቼ ቬለዉ ባልደረባ ክርስቶፍ ሽትራክ እንደሚለዉ ሁለቱ ሰዎችን ቄሱን የገደሉት በጥላቻ ተነሳስተዉ ነዉ።ጥላቻዉ ደግሞ ብዙ ደጋፊዎች አሉት። የሽትራክን አስተያየት ነጋሽ መሐመድ ተርጉሞታል።

መላዉ ዓለምን ያስደነገጠ አረመናዊ እርምጃ ነዉ።ቤተ-ክርስትያን ዉስጥ ይፀልዩ በነበሩ ሽማግሌ ቄስ ላይ የተፈፀመዉ ግድያ፤ ቤተ-እምነቶች ቅዱስ በመሆናቸዉ የተጠለሉባቸዉ ሁሉ ክፉ እንዳይደርስባቸዉ የሚከለክለዉን ነባር ስምምነት የጣሰ ነዉ እርምጃ ነዉ።ሐይማኖት የፀናባትን ፈረንሳይን በጥልቅ የጎዳ አረመናዊ እምጃ ነዉ።ፈረንሳይ የጥንታዊቷ ሮማ የበኩል ልጅ ናት።

ኖርሞንዲ፤ ቡርጉንድ እና ቬንዴ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያንት የታነፁበት አካባቢ ነዉ።ሟቹ አዛዉንቱ ቄስም ከቤተ ክርስቲያን ሊለዩ አይችሉም።ምክንያቱም ሕይወታቸዉ ቤተክርስቲያንን ማገልገልና መፀለይ ነዉና።

Frankreich Hollande mit Vertretern der Religionen Dominique Lebrun mit Kruzifix Symbolbild
ምስል Reuters/B. Tessier

84 ዓመቱ አዛዉንት ፔር ዣክ አሜል ለ58 ዓመታት የሳን ኤትየን ዲዩ ሩቭራይ ቄስ ሆነዉ አገልግለዋል።ከአስር ዓመት በፊት ጡረታ ቢወጡም በማሕበረሰባቸዉ ዘንድ ሩሕሩሕ፤ተግባቢ፤ እና ተራ ሰዉ በመሆናቸዉ የሚደነቁና የሚወደሱ፤ እንደማንኛዉም የፈረንሳይ ገጠራማ አካባቢ ቄስ ደሐ ነበሩ።

ሁለቱ የሽብር መልዕክተኞች ቤተ-ክርስቲያኑ ዉስጥ ገብተዉ፤ አዛዉንቱን ቄስ አንበረከኳቸዉ።ከዚያ ማንቁርታቸዉን በጠሱት።ፀሐፊዉ ክርስቶፍ ሽትራክ እንደሚለዉ አሸባሪዎቹ ሥለሠማዕት ያላቸዉ ግንዛቤ የጎደፈ ነዉ።እየገደሉ «መስዋዕት ሆንን» ካሉ እነሱ ነብሰ ገዳይ ወንጀለኞች ናቸዉ።እንደ እዉነተኛዉ ትርጉም መስዋዕቱ ምንም ሳያጠፉ፤ሲፀልዩ የተገደሉት ፔር ዣክ አሜል ናቸዉ።

ፈረንሳይ እንዲሕ አይነት ነገር ሲያጋጥማት የመጀመሪያዋ አይደለም።እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር በ1996 አልጄሪያ ተራራ ላይ ሰባት መነኮሳት ተገድለዉባታል።ለሟቾቹ በቅርቡ ፓሪስ ዉስጥ መታሰቢያ ሥፍራ ተሰይሞላቸዋል።

ክራኮዉ-ፖላንድ የሚገኙት የሩዎ ጳጳስ ዶሚኒክ ለብራ የቄሳቸዉን መገደል ትናንት ሲሰሙ ክፉኛ ደነገጡ።ግን እንዲሕ አሉ «የካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን ከፀሎትና ከሰዉ ልጆች ወንድማማችነት ሌላ፤ ሌላ መሳሪያ አታዉቅም።ፈረንሳይ ዉስጥ በየቤተ-ክርስቲያኑ ላንድ ቀን በፆም ፀሎት ይዋላል።

ከዚሕ በስተጀርባ ለደረሰዉ ጥፋት አፀፋ ጥፋት በማድረስ የመበቀል አዝማሚያ የለም።የጀርመን ርዕሠ የጳጳሳት ጉባኤ ሊቀመንበር ካርዲናል ራይንሐርድ ማርክስም ተመሳሳይ መልዕክት ነዉ ያሰሙት።«የትናንቱ እርምጃ ከጥላቻ የመነጨ ነዉ።ይሕን መቋቋም አለብን።»ደም ሌላ ደም እንዳይጠራ የሚቻለዉን ሁሉ መደረግ አለበት።

ይሁንና የገዳዮቹ ጭፍን እርምጃ፤ በተለይ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራዉ ቡድን በእንዲሕ አይነቱ ግድያ የመደሰቱ እና ጠብ ማጫሩ ምክንያት አጠያያቂ ነዉ።እርግጥ ነዉ አሚን ማሴይክን የመሳሰሉ የጀርመን ሙስሊሞች የቄሱንም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ ግድያዎችን ያወግዛሉ።አነሱ በሐይማኖች መካካል መቻቻል እንዲኖር ለሚደረገዉ ጥረት ተባባሪ ናቸዉ።

Frankreich Geiselnahme Polizei in Rouen
ምስል picture-alliance/dpa/A. Journois

ግን ፀሐፊዉ እንዚሕ ሙስሊሞች ረዳት የላቸዉም ባይ ነዉ።የሪያድ ምላሽ አልተሰማም።ከዚያ ብዙ ይጠይቃል፤ የሳዑዲ አረቢያ ዋሐቢዝም አሸባሪነትን የሚፃረረዉ መቼ ይሆን? በሳዑዲ አረቢያ ገንዘብ የተመደበላቸዉ መስጊዶች እና ትምሕር ቤቶች ሰባኪዎች ለትክክለኛዉ እስልምና የሚደረግ ዉጊያ የሚባለዉን (እርምጃ) የሚያወግዙት መቼ ነዉ? መለሰም ፀሐፊ ክርስቶፍ ሽትራክ «የአረመኔዎቹ ጥላቻ ብዙ ደጋፊዎች አሉት።ብዙ ተጎጂዎችም አሉት።» ብሎ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ