የፀሐይ አቶማዊ ጋዞችና ሥርጭት
ረቡዕ፣ መጋቢት 8 2002ማስታወቂያ
ይኸው በጋዝ የተሸፈነው አካል የሙቀት መጠኑ ከአንድ ሚልዮን ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ነው።
ፀሐይ ለምድራችን፣ ህይወት አንቀሳቃሹን ብርሃንና ሙቀት ለጋሽ ኮከብ ስትሆን ፣ ከአካሏ፣ የሚፈነጥቁት አቶማዊ ጋዞች ደግሞ አንዳንዴ የምድራችንን ከባቢ አየር ሰንጥቀው የአጭር ሞገድ የራዲዮ ፣ እንዲሁም የቴሌቭዥን ሥርጭቶችን ሊያውኩ ይችላሉ።
በሰው ሠራሽ ሳቴላይቶች አማካኝነት ፣ ከኅዋ የመርከቦችን እንቅሥቃሴ፣የሌላም ቢሆን በተለይ አቅጣጫ ጠቋሚ ምልክቶችን ን ሊያዛቡ ይችላሉ። ያም ሆኖ፣ በፀሐይ ጨረር ሳቢያ በካባቢ አየር ሊፈጠር የሚችለው ፣ ሥርጭትን የሚያውከው ሁኔታ ፣ ሆን ተብሎ የሥርጭት መስመሮችን ለማሠናከል ከሚደረግ ጥረት ፍጹም የተለየ ስለመሆኑ ፣ የዶቸ ቨለ የሥርጭትና በምድር ላይ የሚተከሉ የማሠራጫ አውታሮች አስተባባሪ ክፍል ባልደረባ፤ ሄር ቬርነር ታይስ፣ አስረድተዋል።
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሠ