1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጸጥታው ም/ቤት የዳርፉርን ተልዕኮ አራዘመ

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 23 2003

የተ.መ.ድ የጸጥታዉ ምክር ቤት በሱዳን ዳርፉር ያሰማራዉን የጸጥታ ጥበቃ ጓድ እና የአፍሪቃዉን ህብረት የጥበቃ ጓድ ተልኮ ለአንድ አመት ለማራዘም ወሰነ።

https://p.dw.com/p/RdE3
ምስል AP

በተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ እና በአፍሪቃዉ ህብረት ስር ያለዉ በአጽህሮት UNAMID የተሰኝዉ ጓድ በዳርፉር በጠቅላላ 23.000 ወታደሮች እና 4000 ያህል የሲቪል ሰራተኞችን ያጠቃለለ ሲሆን፣ እ.ጎ.አ 2006 አ.ም የዳርፉር ሰላም ስምምነት ዉል ላይ እንደተጠቀሰዉ የሰላም ጓዱ በዳርፉር የተሰማሩት የጸጥታ አስከባሪ ጓዶች ከሰላም ማስፈን ጥረቱ በተጨማሪ በሰብአዊ ጉዳዪች እና መልሶ ግንባታ ተግባር ፕሮጄ ላይ ግልጋሎት እንደሚሰጥ ተቀማጭነቱን በኒዮርክ ያደረገዉ የተ.መ.ድ ጽህፈት ቤት አስታዉቋል። በዳርፉር ከተሰማራዉ የሰላም አስከባሪ ጓድ መካከል ሃምሳ ያህሉ ጀርመናዉያን ናቸዉ። እ.ጎ.አ 2003 አ.ም በዳርፉር በተቀሰቀሰዉ የእስርበርስ ጦርነት እስካሁን 300.00ያህል ሰዎች ህይወታቸዉን አተዋል 1.8 ሚሊዮን ህዝብ ደግሞ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎአል።

አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን