1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጳጳስ ማርጎት ኬስማን ሰለጣን መልቀቅ

ሐሙስ፣ የካቲት 18 2002

አይጠጡ ከጠጡም አይንዱ ነው ህጉ ። እዚህ ጀርመን ግን ለብዙዎች ምሳሌ መሆን የሚገባቸው አንዲት የሀይማኖት መሪ ይህን ህግ ሳያከብሩ ተይዘው ስራቸውን እስከ መልቀቅ ደርሰዋል ።

https://p.dw.com/p/MBCM
ማርጎት ኬስማንምስል picture alliance / dpa
የጀርመን ፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን ምክር ቤት የመጀመሪያዋ ሴት ሊቀ መንበር ጳጳስ ማርጎት ኬስማን ጠጥተው መኪና ሲነዱ በመያዛቸው ትናንት ከሰዓት በይፋ የጵጵስና ስልጣናቸውን ለቀዋል ። የ51ዓመቷ ኬስማን ከዚህ ዓመት ከጥቅምት ወር አንስቶ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን የጀርመን ፕሮቴስታንት ምክር ቤት ሀላፊነታቸውንና የታህታይ ሳክሰኒ የጵጵስና ስልጣናቸውን ነው የለቀቁት የኬስማን ከስራ መሰናበት የጀርመን ፖለቲከኞችንና የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎችን አሳዝኗል ። ህዝቡ በበኩሉ የተለያየ አስተያየት እየሰጠ ነው ። ለመሆኑ ኬስማን ማናቸው ?