1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ወሰነ።

ቅዳሜ፣ መጋቢት 28 2011

የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ወሰነ።ረቂቅ አዋጁ በምኒስትሮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ተወስኗል።

https://p.dw.com/p/3GOp8
USA halbautomatische Sportgewehre
ምስል picture-alliance/AP Photo/K, Srakocic

የኢትዮጵያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር ረቂቅ አዋጅ እንዲጸድቅ ወሰነ። የጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት በዛሬው ዕለት ባሰራጨው መረጃ መሰረት "ግለሰቦች የታጠቋቸውን የጦር መሳሪያዎች የሕብረተሰቡን ሰላም እና ጸጥታ ለማስጠበቅ ተግባር ሊውሉ የሚችሉበትን ዕድል" ለመፍጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ በምኒስትሮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ተወስኗል። ረቂቅ አዋጁ "በስራ ላይ ባሉ ሕጎች እና አሰራሮች ያልተሸፈኑ ጉዳዮችን በዝርዝር ሕግ መደንገግ እና ወጥነት ያለው ሥርዓት ለመፍጠር" መዘጋጀቱን የጠቅላይ ምኒስትር ፅህፈት ቤት ያሰራጨው መረጃ ያትታል። ኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት ወራት ከፍተኛ ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ገጥሟታል። ትናንት መጋቢት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. እንኳን በአማራ እና አፋር ክልሎች በሚዋሰኑበት ሚሌ ባቲ መገንጠያ ኬላ 990 የክላሽንኮቭ ጥይት መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል። 

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ