1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥንታዊ ሥነ-ጽሑፍ ቅርስ ጥበቃ

ዓርብ፣ ሰኔ 13 2006

በመስጊዶች እና ቤተክርስትያን ዉስጥ የሚገኙ ጥንታዊ ሥነ-ጽሑፎች አብያተ-መጻሕፍት፤ የአንድ ሀገር፤ አህጉር ብሎም የሰዉን ልጅ የእድገት ታሪክ ያዘሉ በመሆናቸዉ እንክብካቤ እና ልዩ ጥበቃ ሊደረግላቸዉ ይገባል።

https://p.dw.com/p/1CMiB

«የበረሀዋ ዕንቁ» በመባልም ወደ ምትታወቀዉ ወደ ምዕራብ አፍሪቃዊትዋ ማሊ፤ ቲምቡክቱ ከተማ፤ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በቅርስነት እጎአ 1988 ተመዝግባለች። በውስጧ ያሉት ጥንታዊ መስጊዶች እና አብያተ-መፅሐፍት ስለ ቲምቡክቱ ታሪካዊነት እና ጥንታዊነትም ይመሰክራሉ። ይህም ስፍራ የአገር ጎብኝዎች መስብ ነበር። ግን በሰሜናዊ ማሊ የሚንቀሳቀሰዉ አክራሪዉ እስላማዊ ቡድን ፍላጎት፤ ጥንታዊትዋን የምራዕራብ አፍሪቃ የባሕል እና የቅርስ ማዕከል ቲምቡክቱን፤ ማጥፋት ነዉ። በሰሜናዊ ማሊ የሚገኙና በዘመናት የሚቆጠር እድሜ ያላቸዉን ጥንታዊና ታሪካዊ የሥነ- ጽሑፍ ቅርሶች በአብዛኛዉ፤ ይዞታቸዉ በከባድ ሁኔታ የተበላሸ ነዉ። እነዚህ ቅርሶች ታሪካዊ መረጃቸዉ በጽንፈኛዉ ቡድን ጥቃት ቸርሶ እንዳይጠፋ፤ ነዋሪዎች ከከተማዋ በድብቅና በፈቃደኝነት ወደ ማሊ መዲና ባማኮ እያሸሹ ይገኛሉ። እነዚህ በድብቅ ባማኮ ከተማ ላይ በድብቅ የደረሱት ጥንታዊ ሥነ- ጽሑፎች፤ ታሪካዊነታቸዉ ተጠብቆ ለትዉልድ እንዲሻገር፤ ከጀርመን ሃንቡርግ ዩንቨርስቲ በመጡ ምሁራን፤ እየታደሱ ቅርስነታቸዉ ተጠብቆ እንዲቆይ እየተደረገ ነዉ።