1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥበብ እመቤት አርቲስት አርቲስት ዘነበች ታደሰ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 22 1999

ኢትዮጽያ ካፈራቻቸዉ ድንቅና ዉብ የመድረክ ሰዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት የምትገኝ የጥበብ ሰዉ ነበረች፣ ተፈጥሮ በቸረቻት ችሎታዋም ለአመታት በዉስጥዋ የታመቀዉን የቲያትር እና የሙዚቃ ፍቅር በህዝብ ፊት ቆማ በማሳየትዋ ትልቅ ደስታን እንደሚሰጣት ደጋግማ ትናገር ነበር

https://p.dw.com/p/E0mN
ለበርካታ አመታት ከመድረክ ተለይታ የማታዉቅ አንጋፋዋ የጥበብ እመቤት አርቲስት ዘነበች ታደሰ ዘንድሮ የአዲስ አበባዉ ብሄራዊ ትያትር ሃምሳኛ አመት የምስረታ በአሉን ባከበረበት ወቅት ሎሚ ብወረዉር የተሰኘዉን ዜማዋን አቅርባለች። በብዙዎቻችን ዘንድ ጭራቀረሽ በሚለዉ በቅጽል ስሟ የምናቃት አርቲስት ዘነበች በድንገተኛ ህመም መጋቢት ሰባት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። በድንገት ከዚህ የተለየችዉ የአርቲስት ዘነበች ታደሰ የአርባ ቀን መታሰያ ወዳኦችዋ አፍቃሪዎችዋ ዘመዶችዋ በተገኙበት ታስቦ ዉሎአል። ስለ አንጋፋዋን የጥበብ እመቤት ዘነበች ታደሰ ከደራሲ ተዉኔት እና ገጣሚ አያልነህ ሙላት ጋር እናወሳለን