የጥረት ኮርፖሬሽን ም/ሃላፊ ጉዳይ
ዓርብ፣ ጥር 24 2011ማስታወቂያ
የጥረት ኮርፖሬሽንን ላልተገባ ወጪ ዳርገዋል የተባሉት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ምትኩ በየነ ተከስሰው ዛሬ ፍርድ ቤት ቢቀርቡም ጉዳያቸው የፊታችን ሰኞ እንዲታይ ተወስኗል። ዛሬ ጉዳያቸውን ሊመለከት የነበረው የባህር ዳርና አካባቢው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ለሰኞ ከሰዓት እንዲቀርቡ የወሰነው የባህርዳሩ ወኪላችን አለምነው መኮንን እንደዘገበው በጊዜ መጣበብ ምክንያት ነው። ሆኖም ፍርድ ቤቱ የቀሪ አራት ተጠረጣሪዎችን ጉዳይ ዛሬ ተመልክቷል። ዝርዝሩን ካባህርዳር አለምነው መኮንን ልኮልናል።
አለምነው መኮንን
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ