1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥላቻ ወንጀል በብሪታንያ

ሰኞ፣ ሐምሌ 18 2008

ብሪታንያ ውስጥ በርዕሰ ከተማዋ በለንደን ፣በሊቨርፑል እና በሌስተር ከተሞች የዘር ፣የሃይማኖት ፣የቀለም ልዩነትን መቀበል በማይፈልጉ ፅንፈኛ ብሪታንያውያን የሚፈፀመው ወንጀል ቁጥር ጨምሯል ።

https://p.dw.com/p/1JVfx
Großbritannien Fremdenfeindlichkeit Protest
ምስል picture alliance/ZUMA Press/V. Flores

[No title]


ከምዕራባውያን ሃገራት መካከል በአሁኑ ጊዜ ብሪታንያ ዘረኝነት የከፋባት ሃገር መሆንዋን በቅርቡ ይፋ የተደረገ አንድ ዘገባ አስታውቋል ። እንደ መረጃው በብሪታንያ ከጀርመን አስር እጥፍ የሚበልጥ ከአሜሪካን ደግሞ በአምስት ጊዜ የሚልቅ የፅንፈኝነት ወንጀል ተመዝግቧል ። ብሪታንያ ውስጥ በርዕሰ ከተማዋ በለንደን ፣በሊቨርፑል እና በሌስተር ከተሞች የዘር የሃይማኖት የቀለም ልዩነትን መቀበል በማይፈልጉ ፅንፈኛ ብሪታንያውያን የሚፈፀመው ወንጀል ቁጥር ጨምሯል ። በተለይ የብሪታንያ ህዝብ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ከወሰነ በኋላ የተባባሰውን ይህንኑ ወንጀል ለመከላከል የብሪታንያ መንግሥት 2.4 ሚሊዮን ፓውንድ መድቧል።


ሃና ደምሴ


ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ