1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚሩ የቀብር ሥነ-ስርአት ተፈጸመ

እሑድ፣ ነሐሴ 27 2004

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር በዛሬው ዕለት በይፋ የሃዘን ስነ ስርዓት ተፈጸመ። የሟቹ አስከሬን በብዙ ሺህ ሃዘንተኞች ታጅቦ ወደ መስቀል አደባባይ ካመራ በኋላ በዚያው በተካሄደው መንግሥታዊ የሃዘን ስነ ስርዓት ላይ በርካታ የአፍሪቃ መሪዎችና ዓለምአቀፍ ልዑካን መገኘታቸውን የዜና ምንጮች አመልክተዋል።

https://p.dw.com/p/162La
ምስል REUTERS

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ቀብር በዛሬው ዕለት በይፋ የሃዘን ስነ ስርዓት ተፈጸመ። የሟቹ አስከሬን በብዙ ሺህ ሃዘንተኞች ታጅቦ ወደ መስቀል አደባባይ ካመራ በኋላ በዚያው በተካሄደው መንግሥታዊ የሃዘን ስነ ስርዓት ላይ በርካታ የአፍሪቃ መሪዎችና ዓለምአቀፍ ልዑካን መገኘታቸውን የዜና ምንጮች አመልክተዋል። አቶ መለስ ዜናዊ ቤልጂግ ውስጥ በህክምና ላይ እንዳሉ ማረፋቸው የተነገረው ከአሥር ቀናት በፊት ነበር። የአንዴው የዓማጺያን መሪ የደርግ አገዛዝ ከወደቀ ወዲህ ሥልጣን በመያዝ ለ 21 ዓመታት በአስተዳደር ላይ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው። የአቶ መለስ ቀብር ዛሬ ከቀትር በኋላ ይፋውን የሃዘን ስነ ስርዓት ተከትሎ በቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ተከናውኗል።

በአዲስ አበባ የቀብር ሥነ-ስርአቱን ሂደት እንዲሁም በዉጭ ያሉ ኢትዮጵያዉያን የሃዘን ሥነ-ስርአቱን በምን ሁኔታ አሳለፉ? ከሳዉዲ አረብያ፣ ከለንደን እንዲሁም ከዩናይትድ ስቴትስ አጠር ያሉ ዘገባዎችን አሰባስበናል።

አዜብ ታደሰ

መስፍን መኮንን

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ