1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የኬንያ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ሰኔ 15 2008

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የኬንያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል ። 35 ተኛው የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም ሁለቱ ሃገራት ከአራት ዓመት በፊት የተፈራረሙት ልዩ የሁለትዮሽ ስምምነት በአፋጣኝ ተግባራዊ በሚሆንበት መንገድ ላይ መክሯል ።

https://p.dw.com/p/1JBO5
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል Getty Images

[No title]



የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኬንያ የሦስት ቀናት ይፋ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ናይሮቢ ይገባሉ ። አቶ ኃይለማርያም ኬንያ የሚሄዱት የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የንግዱን ማህበረሰብ አባላት አስከትለው ነው ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያምና የንግዱ ማህበረሰብ አባላት የሁለቱን ሃገራት የንግድ ግንኙነት የማጠናከር ዓላማ ባለው የኬንያ እና የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ መድረክ ላይ እንደሚሳተፉ ተገልጿል ። ትናንት የተካሄደው 35 ተኛው የኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባም ሁለቱ ሃገራት ከአራት ዓመት በፊት የተፈራረሙት ልዩ የሁለትዮሽ ስምምነት በአፋጣኝ ተግባራዊ በሚሆንበት መንገድ ላይ መክረዋል ። ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የኬንያ ጉብኝት እና ስለ ኢትዮ-ኬንያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ስብሰባ የናይሮቢውን ዘጋቢያችንን ፋሲል ግርማን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር ።
ፋሲል ግርማ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ