1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመቀሌ ጉብኝት

ዓርብ፣ ሚያዝያ 5 2010

አዲሱ የኢትዮጵያ  ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ  ዛሬ መቀሌ ተገኝተው ከክልሉ ሃላፊዎችና እና ከህብረተሰቡ ጋር ተወያዩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ ባሰሙት ንግግር  የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ መንግስታቸው ከክልሉ አመራር ጋር ተባብሮ እንደሚሰራ ቃል ገብተዋል።

https://p.dw.com/p/2w1Ka
Äthiopien Premierminister Dr. Abiy Ahmed
ምስል Office of the Prime Minister-Ethiopia

MMT-PM Mekele Besuch und Beschwerde von positionen - MP3-Stereo

የትግራይ ህዝብም  በሰላም እና ልማት ላይ እንዲያተኩር ጥሪ አቅርበዋል። ከዚያ ቀደም ሲል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በሚገኘዉ የሰማዕታት ሃዉልት ሥር ጉንጉን አበባ አኑረዋል። በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የሰማዕታት ሐውልት አዳራሽ የተካሄደውን ውይይት የተከታተሉት በመቀሌ ከተማ የግሎባል የጋዜጠኝነት ኮሌጅ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብረሃ ገብረአረጋዊ እንደነገሩን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው በይበልጥ የኢትዮጵያን አንድነት አጉልተው አንስተዋል።በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር የተደመሙት አቶ አብርሃ የተባለው ተግባራዊ ሲሆን ማየት ነዉ የቀረን ሲሉ ተናግረዋል። በሌላ በኩል አረና ትግራይ የተባለው ተቃዋሚ ፓርቲ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ማህበረሰቡን ሁሉ ያካተተ አይደለም ሲል ቅሬታዉን ገልፆአል።

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ