የጎደሬ ደን ዛሬም ያነጋግራል
ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 2003ማስታወቂያ
ክብካቤና ጥበቃ የሚደረግለት ከሶስት ሺህ ሄክታር በላይ የተፈጥሮ ደን የሸነዉ መሬት ለባለሃብት መሰጠቱ የአካባቢዉ ኗሪዎችንም ሆነ የአካባቢ ተፈጥሮ ተሟጋቾችን ቅሬታ አስነስቶ ሲያነጋግር ከርሟል። ጉዳዩ ወደከፍተኛ መንግስት ባለስልጣናትም ዘንድ ደርሶ ዳግም እንዲጠና ተጠይቋል። ዛሬም የዚህ ወደ አስራ አራት ወንዞች ይመነጩበታል የተባለ ጥቅጥቅ የተፈጥሮ ደን ጉዳይ እልባት አላገኘም። የአካባቢዉ ኗሪዎች አቤቱታቸዉን እያሰሙ ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ