1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግንቦት 7 1997 ቱ ምርጫ አራተኛ አመት

ዓርብ፣ ግንቦት 7 2001

የምርጫዉ ዉጤትና መዘዙ ግን በርግጥ የመሰለዉን ሁሉ ከመመስል አላሳለፈዉም። አራተኛ አመቱ ዛሬ ሲዘከር ዉጪ የሚኖረዉን ኢትጵያዊ ለሰላማዊ ሰልፍ-አሳድሞት፥ የዉስጡን በቅይጥ ስሜት አጅሎት ነዉ-የዋለዉ

https://p.dw.com/p/HrIk
የሙርሲ ነገድ አባላት ድምፅ ሲሰጡ-1997ምስል DPA

ግንቦት ሰባት 2001-እንደምን ዋላችሁ።ከአራት አመት በፊት የዛሬን ዕለት ኢትዮጵያ ዉስጥ የተደረገዉ ምርጫ በዚያች ሐገር የዘመነ-ዘመናት ታሪክ አዲስ በጎ የዲሞክራሲ ተስፋ ፈንጣቂ ክስተት መስሎ ነበር።የምርጫዉ ዉጤትና መዘዙ ግን በርግጥ የመሰለዉን ሁሉ ከመመስል አላሳለፈዉም። አራተኛ አመቱ ዛሬ ሲዘከር ዉጪ የሚኖረዉን ኢትጵያዊ ለሰላማዊ ሰልፍ-አሳድሞት፥ የዉስጡን በቅይጥ ስሜት አጅሎት ነዉ-የዋለዉ።የግንቦት 97ቱ ምርጫ፥ ደም አፋሳሽ ዉጤቱ፥ የአራት አመት አጓጉል ጉዞዉን እና ለኮርሞ በታቀደዉ ምርጫ ላይ የሚኖረዉን አስተጋብኦት በተመለከተ ከበርሊን፥ ከለንደን፥ ከአዲስ አበባና ከዚሕ ከቦን የተጠናቀሩ ዘገባዎችን በቅደም ተከተል ያዳምጡ።የገዢዉን ፓርቲ የኢሕአዴግን ባለሥልጣናት ወይም አባላት ለማነጋገር ያደረግ ነዉ ሙከራ አልተሳካልንም።

Parlamentswahl in Äthiopien (hier: Anhänger der Regierungspartei)
ከምርጫዉ በፊት-የአዲስ አባባ ስልፍኛምስል AP

ነጋሽ መሐመድ