1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግንቦት ሰባት ተጠርጣሪዎች ችሎት ውሎ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 28 2001

የኢትዮጵያ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ዓቃቤ ህግ ክስ የመሰረተባቸውን የግንቦት ሰባት አባላት ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ ዛሬ ሲመለከተው ዋለ።

https://p.dw.com/p/J3Tt

ችሎቱ ዓቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎች ላይ አለኝ ያለውን የምስክሮችና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ በመጨረሱ በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ቀጥሮ ይዞ እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ በነዚሁ ተጠርጣሪዎች ላይ የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ሰፊና ውስብስብ በመሆኑ ገና የመጨረሻ ስራ እንደቀረው በማመልከት ለፊታችን ሀሙስ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዞ የዛሬውን ውሎውን አብቅቶዋል።

ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ/ተክሌ የኋላ