1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግብፅ ህዝበ ውሳኔ ውጤትና አንድምታው

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2005

ተቃዋሚዎች አሁንም ረቂቁን ህግ ለእስልምና በጣም ያደላና ኢ ዲሞክራሲያዊ እንዲሁም ለአናሳ የህብረተሰብ ክፍሎች ከለላ የማይሰጥ ሲሉ ይቃወሙታል። የግብፅን ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያሰረው ብጥብጥና አለመረጋጋት እንዲያበቃ ህጉ ወሳኝ ነው የሚሉት ሙርሲ ግን ይህን አይቀበሉም ።

https://p.dw.com/p/179Dq
ምስል Reuters

በግብፅ አዲሱ ረቂቅ ህገመንግስት መፅደቁ ከዓመት በፊት የተካሄደዉን አብዮት ሃይማኖትና ፖለቲካን በመቀላቀል ይጎዳዋል ሲሉ የሐገሪቱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችዎች አሳሰቡ። ዜጎችን በደጋፊና በተቃዋሚ ጎራ ከፍሎ ሲያወዛግብ የቆየዉና ሕዝብ ድምፁን የተሰጠበት ህገመንግስት 64በመቶ ድምፅ ማግኘቱ ትናንት ይፋ መሆኑ ከተገለፀ በኋላ አመፅ የተቀላቀለዉ ተቃዉሞ ታይቷል። የህዝበ ዉሳኔዉ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ተጭበርብሯል የሚሉት ወገኖች በሙስሊም ወንድማማቾች መሪነት የቀረበዉን ህገመንግስትም ሆነ የተነገረዉን ዉጤት እንደማይቀበሉት ነዉ በድጋሚ ያመለከቱት። ለተቃዉሞ ከወጡት አንዱ፤
«አብዮቱ እንደሚቀጥል እና ህገመንግስቱ እንደማይኖር ለመግለፅ እፈልጋለሁ። ህገመንግስቱ ሁሉም ህዝብ የሚስማማበት መሆን ይኖርበታል እንጂ በግብፃዉያን መካከል መከፋፈልን የሚፈጥር መሆን የለበትም።።»

ፕሬዝደንት ሞሐመድ ሙርሲ የህዝበ ዉሳኔዉ ዉጤት ይፋ ሲሆን ትናንታዉኑ ህገመንግስቱን በፊርማቸዉ አፅድቀዋል። የፊታችን ቅዳሜም በጸደቀዉ ህገመንግስት መሠረት ሙሉ የህግ ማዉጣት ስልጣን ላገኘዉ ላዕላይ ምክር ቤት ንግግር ያደርጋሉ። በቀጣይ ሁለት ወራት ዉስጥ የታህታይ ምክር ቤቱ ምርጫ እንደሚካሄድም ይጠበቃል። የሙስሊም ወንድማማቾች የፖለቲካ ክንፍ ከሆነዉ የነፃነትና የፍትህ ፓርቲ ሙራዲ አሊ፤
«ለቀጣዩ ምክር ቤት የህዝብ ጉባኤን ለመምረጥ የሚረዱ አንዳንድ ህጎችን መቅረፅ ይኖርብናል፤ ይህም ለእኛ ቀዳሚዉ ጉዳይ ነዉ። በተጨማሪም የኤኮኖሚ ማሻሻያ ለማድረግ ምን ዓይነት በአፋጣኝ ያስፈልጋሉ በሚለዉ ላይ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋ እንወያያለን።»
የግብፅ ባለስልጣናት ትኩረት አሁን የሀገሪቱን ምጣኔ ሃብት ይዞታ ሆኗል። ሙርሲ ድጋፍ ለመጠየቅ ወደጀርመን እንደሚመጡም ተጠቁሟል።

Bildergalerie Verfassungsreferendum in Ägypten Mursi 2012
ምስል AP
Bildergalerie Verfassungsreferendum in Ägypten Mursi 2012
ምስል Reuters

የብዙሃኑን ድምፅ ያገኘውን የግብፅ ረቂቅ ህገ መንግሥት የግብጹ ፕሬዝዳንት መሐመድ ሙርሲ ትናንት ማምሻውን አፅድቀዋል ። ረቂቁ ከአረቡ ዓለም በህዝብ ብዛት ቀዳሚውን ስፍራ በምትይዘው በግብፅ ህዝብ መካከል ከፍተኛ መከፋፈልን አስፍኖ ቆይቷል ። ተቃዋሚዎች አሁንም ረቂቁን ህግ ለእስልምና በጣም ያደላና ኢ ዲሞክራሲያዊ እንዲሁም ለአናሳ የህብረተሰብ ክፍሎች ከለላ የማይሰጥ ሲሉ ይቃወሙታል ። የግብፅን ኤኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያሰረው ብጥብጥና አለመረጋጋት እንዲያበቃ ህጉ ወሳኝ ነው የሚሉት ሙርሲ ግን ይህን አይቀበሉም ። ስለ ግብፅ ህዝበ ውሳኔ ውጤትና አንድምታው የጅዳው ወኪላችንን ነበዩ ሲራክን በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ