1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሪክና የአበዳሪዎች ፍጥጫ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 9 2007

ግሪክ ከአበዳሪዎች ይለቀቅልኛል ብላ የምትጠብቀው ብድር ጉዳይ እስካሁን መላ አልተገኘለትም ። ግሪክና አበዳሪዎቿ ገንዘቡ በሚሰጥበት ቅድመ ግዴታዎች ላይ መስማማት አልቻሉም ። የግሪክና የአበዳሪዎች ፍጥጫ እንዲሁም የግሪክ እጣ ፈንታ የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

https://p.dw.com/p/1FiC3
Belgien Treffen Merkel, Hollande, Tsipras
ምስል Guido Bergmann/Bundesregierung/dpa

የግሪክና የአበዳሪዎች ፍጥጫ

ትሮይካ በመባል የሚጠሩት ሶስቱ የግሪክ አበዳሪዎች ማለትም የዩሮ ተጠቃሚ ሃገራት ፣ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክና ዓለም ዓቀፉ የገንዘብ ድርጅት IMF ግሪክን ከገንዘብ ቀውስ ለመታደግ የመጀመሪያውን ብድር ከሰጡ 5 ዓመት አለፈ ።ያኔ አበዳሪዎቹ ገንዘቡን የሰጡት ግሪክ ማሟላት አለባት ያሏቸውን ቅድመ ግዴታዎች በማስቀመጥ ነበር ። ቅድመ ግዴታዎችም በጥቅሉ ግሪክ የኤኮኖሚ የተሃድሶ እርምጃዎችን እንድትወስድ እንዲሁም የመንግሥት ንብረቶችን ወደ ግል ይዞታ እንድታዛውር የሚጠይቁ ናቸው ። የያኔው የግሪክ መንግሥትም የተጠየቀውን ለማሟላት በገባው ቃል መሠረት የብድሩ መርሃ ግብር ቢቀጥልም በጎርጎሮሳውያኑ 2015 ዓም መጀመሪያ ላይ አዲስ መንግሥት ከተቋቋመ በኋላ ግሪክና አበዳሪዎቿ ብድር በሚፈቀድበት መንገድ ላይ መወዛገባቸው አልቆመም ። አዲሱ የግሪክ መንግሥት ሃገሪቱ አለ አግባብ ተጭነውባታል የሚላቸውን ግዴታዎች አስቀራለሁ ሲል ለመራጩ ህዝብ የገባውን ቃል ለመፈፀም ከአበዳሪዎች ጋር በተለያዩ ጊዜያት ድርድሮች ቢያካሂድም እስካሁን አልተሳካለትም ። የግሪክ አበዳሪዎች ግሪክ የኤኮኖሚ ተሃድሶ እርምጃዎችን ለመውሰድ በማቅማማትዋ ሃገሪቱን ከገንዘብ ቀውስ ለመታደግ ከታቀደው ብድር የመጨረሻውን 7.2 ቢሊዮን ዩሮ ለመልቀቅ አልተስማሙም። ለሳምንታት የዘለቀው ይህ የግሪክና የአበዳሪዎቿ ፍጥጫ ግሪክን ከዩሮ ተጠቃሚ አባል ሃገራትማህበር እስከ መውጣት ሊያደርሳት ይችል ይሆናል የሚሉ አስተያየቶችne እያሰነዘረ ነው ። በርሊን ነዋሪ የሆኑት የኤኮኖሚ እድገት መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም የኤኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪ ዶክተር ፈቃዱ በቀለ የፍጥጫውን መንስኤ ይገልጹልናል ።
ግሪክ ከዩሮ ለቃ ትውጣ የሚሉት ወገኖች ከቀድሞው አሁን ቁጥራቸው እየጨመረ ነው ። ጫናው በረታብኝ የምትለው ግሪክም በጀርባም ቢሆን እንደምትለው ዩሮን ትታ የራስዋን የመገበያያ ገንዘብ መጠቀም ብትጀምር ዶክተር ፈቃደ እንደሚሉት ከባድ ችግር ውስጥ ልትወድቅ መቻሏ ሳይታለም የተፈታ ነው ። ችግሩ ደግሞ በግሪክ ብቻ ሳይወሰን አበዳሪዎችንም ለኪሳራ የሚዳርግ እርምጃ ነው የሚሆነው ።
በሌላ በኩል ለግሪክ የሚበጀው ከዩሮ ማህበር መውጣቷ ነው ብለው የሚከራከሩ ወገኖች ግን ይህ በረዥም ጊዜ የሃገሪቱን ኤኮኖሚ ሊያሳድግ የሚችል ነው ብለው ያምናሉ ።

ዶክተር ፈቃደ አስተያየት ት ምንም እንኳን በይፋ በሚካሄዱት ንግግሮች ስምምነት ላይ ባይደረስም አበዳሪዎች በዝግ በተካሄደ ድርድር ከግሪክ እዳ የተወሰነው ለመሰረዝ ተስማምተዋል ።ይሁንና በርሳቸው አባባል የእዳ ቅነሳው ወይም ማስተካከያው የአሁኑን የግሪክን ችግር ለማቃለል የሚፈይደው ነገር አይኖርም ።
ድምፅ 2
ግሪክ ቃል የተገባላትን ብድር ያዘገየባት አበዳሪዎች ያስቀመጡዋቸው ቅድመ ግዴታዎች ዶክተር ፈቃደ እንደሚሉት ህጋዊ ያልሆነ ጫና ነው ። ይህ ጫናም የሃገሪቱን ኤኮኖሚ ሊያሳድግ አልቻለም ።
ኂሩት መለሰ

Griechenland Grexit Symbolbild
ምስል picture-alliance/dpa/B. Roessler
Griechenland Yanis Varoufakis und Alexis Tsipras im Parlament in Athen
ምስል L. Gouliamaki/AFP/Getty Images

አርያም ተክሌ