1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መረጃ የማግኘት ችግር

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2011

የቀድሞው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ከፈረሰ ወዲህ መረጃ የማግኘት ችግር መባባሱን ጋዜጠኞች ለዶቼቬለ ተናግረዋል። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ስለ ወቀሳው የቀድሞውን የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ የወሰደው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክረታርያት አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠይቅም ለዛሬ መልሱ አልደረሰውም።

https://p.dw.com/p/3GYsV
Diskussion über Medienreformen in Äthiopien
ምስል DW/Y. Gebreegziabhe

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከመንግሥት መረጃ ማግኘት አዳጋች እየሆነ መምጣቱን ጋዜጠኞች ተናገሩ። በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን የተለያዩ እድሎች እና ተግዳሮቶች ላይ አትኩሮ ትንንት እና ዛሬ በአፍሪቃ ኤኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በተካሄደው ዐውደጥናት ላይ የተሳተፉ ጋዜጠኞች  በተለይ የቀድሞው የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ከፈረሰ ወዲህ ችግሩ መባባሱን ለዶቼቬለ DW ተናግረዋል። የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ስለ ወቀሳው የቀድሞውን የመንግሥት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሥራ የወሰደው ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክረታርያት አስተያየት እንዲሰጥ ቢጠይቅም ለዛሬ መልሱ አልደረሰውም።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር  
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ  

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ