1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገንዘብ ቀውስ #ላይ ያተኮረው የአውሮፓ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ

ዓርብ፣ ጥቅምት 7 2001

ከአሜሪካን ተነስቶ አውሮፓ እና እስያን ያዳረሰው የገንዘብ ቀውስ ትናንት ብራሰልስ ቤልጅየም የተከፈተው የሀያ ሰባቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሪዎች ጉባኤ ዋነኛ የመነጋሪያ ርዕስ ነበር ።

https://p.dw.com/p/FcHR
የህብረቱ ኮሚሽነር ጆሴ ማኑዌል ባሮሶ እና የወቅቱ የህብረቱ ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዞምስል AP
በአናት የመጣው የገንዘብ ቀውስ የጉባኤውን ቀልብ ይሳብ እንጂ ከወራት በፊት አስቀድሞ በተያዘው አጀንዳ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለመከላከል ከዚህ ቀደም አባላት የተስማሙባቸውን ዝርዝር ነጥቦች ና የአየርላንድ ህዝብ በህዝበ ውሳኔ ውድቅ ያደረገው የተሻሻለው የሊዝበኑ ውል ላይ ለመወያየት ነበር የታቀደው ።