1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጅቡቲ ሴቶች የረሐብ አድማ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 28 2008

ከአሥር የሚበልጡት ሴቶች እንደሚሉት ጦር ሐይሉ በሐገራቸዉ ሴት ዜጎች ላይ የሚፈፀመዉ ግፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረከተ እና እየተጠናከረ ነዉ

https://p.dw.com/p/1IjK6
ምስል Getty Images/S.Gallup

[No title]

ብራስልስ-ቤልጂግ የሚኖሩ የጅቡቲ ተወላጆች፤ የጅቡቲ ጦር ሠራዊት ባልደረቦች በሐገሪቱ ሴቶች በተለይም በአፋር ጎሳ ሴቶች ላይ ይፈፅሙታል ያሉትን የመድፈር ወንጀል በመቃወም የረሐብ አድማ መትተዋል።ከአሥር የሚበልጡት ሴቶች እንደሚሉት ጦር ሐይሉ በሐገራቸዉ ሴት ዜጎች ላይ የሚፈፀመዉ ግፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረከተ እና እየተጠናከረ ነዉ።የጅቡቲ መንግሥት ወታደሮቹ የሚያደርሱትን ግፍ ያስቆም ዘንድ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ግፊት እንዲያደርግበትም ጠይቀዋል።ሴቶቹ የረሐብ አድማዉን ከመቱ አሥር ቀን አልፏቸዋል።የብራስልሱ ወኪላችን ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ