1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪው እና የኢ.ሰ.መ.ኮ. መግለጫ

ዓርብ፣ የካቲት 19 2013

የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ,ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በስመረቀበት መድረክ  እነ ጃዋር መሐመድ ከእስር እንዲፈቱ የጠየቀውን  ተመራቂ  ፍርድ ቤት ቢያሰናብተውም  ጠበቃው እንደታሰረ እንደሚገኝ አመለከቱ።

https://p.dw.com/p/3pye6
Äthiopien EHRC  LOGO

«ኢሰመኮንም አሳስቦታል»

የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ,ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በስመረቀበት መድረክ  እነ ጃዋር መሐመድ ከእስር እንዲፈቱ የጠየቀውን  ተመራቂ  ፍርድ ቤት ቢያሰናብተውም  ጠበቃው እንደታሰረ እንደሚገኝ አመለከቱ። የመሐመድ ዴክሲሶ ጠበቃ ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ደንበኛቸው በመድረኩ የተናገረው የመናገር ነጻነት አንዱ ማሳያ ቢሆንም ሁከት በማነሳሳት እና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው በሚል ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ ታስሯል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩ እንዳሳሰበው ባመለከተበት መግለጫው ፍርድ ቤት ተመራቂው የጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲለቀቅ የሰጠው ውሳኔ እንዲከበር ጠይቋል።

ስዩም ጌቱ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ