1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ፕሬዚደንት ዳግም መመረጥ

ሰኞ፣ ግንቦት 17 2001

የጀርመን ፕሬዚደንት ሆርስት ከለር ሀገሪቱን እንደገና ለሁለተኛ የአምስት ዓመት የስልጣን ዘመን በርዕሰ ብሄርነት እንዲመሩ ባለፈው ቅዳሜ መመረጣቸው ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/Hx5H
ምስል AP

በምክር ቤት በተካሄደው የጀርመን ፌዴራዊ ምክር ቤት እንደራሴዎችና የክፍላተ ሀገር ውክልና ምክር ቤት አባላት በተሳተፉበት ፕሬዚደንታዊ ምርጫ ስነ ስርዓት ላይ ስድስት መቶ አስራ ሶስት ድምጽ በማግኘት ለሁለተኛ ጊዜ የተመረጡት ፕሬዚደንት ከምርጫው በኋላ ባሰሙት ንግግራቸው የሀገሪቱ መሪ በቀጥታ በህዝብ እንዲመረጥ ያሰሙት ሀሳብ በወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና ተንታኞችን ማነጋገር ይዞዋል።

ይልማ ሀይለሚካኤል/አርያም ተክሌ