1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን የልማት ተራድኦ

ዓርብ፣ መጋቢት 10 2002

በዓለም ላይ የልማት ዕርዳታ በመስጠት ከዩናይትድ ስቴትስ ቀጥሎ ጀርመን ሁለተኛዋ ሀገር ናት ። ብሪታኒያ ፈረንሳይ እና ጃፓን ከጀርመን ቀጥሎ በሶሶተኛ በአራተኛ እና በአምስተኛ ደረጃ የሚቀመጡ የልማት ዕርዳታ ለጋሽ ሀገራት ናቸው ።

https://p.dw.com/p/MXfh

የጀርመን መንግስት የልማት ዕርዳታ ተግባራትን በዋነኛነት የሚያከናውነው በ 3 መስሪያ ቤቶች አማካይነት ነው ። እነርሱም በእንግሊዘኛው ምህፃር GTZ በመባል የሚጠራው የጀርመን የቴክኒክ ተራድኦ ድርጅት፣ በምህፃሩ DED የተሰኘው የጀርመን የልማት ዕርዳታ ድርጅት እንዲሁም KfW በሚል ምህፃር የሚታወቀው የጀርመን የመልሶ ግንባታ አባዳሪ ባንክ ናቸው ። የጀርመን መንግስት የዕርዳታ ድርጅቶች በአንድ ማዕከል እንዲዋቀሩ ለማድረግ ካሰበ ቆየት ብሏል ። ወጪና ገቢን የሚቆጣጥረው የፌደራሉ መንግስት መስሪያ ቤት እንደሚለው 1400 የሚሆኑ ሰራተኞች በ 3ቱ መስሪያ ቤቶች ውስጥ አላስፈላጊና ተደጋጋሚ በሆነ መዋቅር ነው የሚሰሩት።

ዳንኤል ሼሽከቪች፤ ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ