1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ዉህደት 21ኛ ዓመት በዓል በቦን

ሰኞ፣ መስከረም 22 2004

በአዉሮጳዉያኑ 1961ዓ,ም ነሐሴ 13 ማለዳ በርሊኖች ከእንቅልፋቸዉ ሲነሱ ያዩት አስደንጋጭ ህልም እንጂ እዉን አልመሰላቸዉም ነበር። ሌሊቱን ተገንብቶ ምስራቅ ምዕራብ ብሎ ጀርመንን ለዓመታት የከፈለዉ ግንብ ቤተሰብ ከቤተሰብ፤ ወዳጅ ከዘመድ፤ ሥራን ከሠራተኛ ሳይቀር አለያየ።

https://p.dw.com/p/RopU
የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት በቦንምስል dapd

ዛሬ ግንቡ ከፈረሰ 21ኛ ዓመቱ በቀድሞዋ የምዕራብ ጀርመን ዋና ከተማ ቦን ሲከበር ቤቱ የቀረ ሰዉ የለም በሚያስብል መልኩ ለወትሮ ጭር የሚሉት ጎዳናዎች ብሩህ ፊት በተላበሱ ወገኖች ተሞልተዋል። በዓሉ በየዓመቱ በተለያዩ ፌደራል ግዛት የሚስተናገድ ሲሆን የዘንድሮዉ ባለተራ ዶቼ ቬለ ራዲዮ የሚገኝበት የኖርድራይን ቬስት ፋለን ግዛት ነዉ። ከተማዉ ደግሞ ቦን። ለበዓሉ ድምቀት የተለያዩ ዝግጅቶች ከቅዳሜ ዕለት አንስቶ ሲካሄዱ ቆይተዋል፤ ቦን ነፃነት፤ አንድነትና ፍስሐ በሚል መፈክር እንግዶቿን ማስተናገዱን ተያይዛዋለች። ዝግጅቱ ከሚከናወንባቸዉ አካባቢዎች በአንዱ የተገኘችዉ ባልደረባዬን አዜብ ታደሰን ከቀትር በኋላ ስለበዓሉ አከባበር ያየችዉን እንድታካፍለን በስልክ አነጋግሬያታለሁ።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ