1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ መታሰቢያ

ዓርብ፣ ኅዳር 1 2010

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች እንዳሉት በሚቀጥሉት ዓመታት የአውሮጳ ህብረት ተጠራጣሪነትን እና ተቃውሞን ከመስፋፋት ማስቆሙ አስፈላጊ እና በአስቸኳይ መፈፀምም ያለበት ጉዳይ ነው።

https://p.dw.com/p/2nQV0
Frankreich Emmanuel Macron mit Frank-Walter Steinmeier PK im Elysee Palast, Paris
ምስል picture-alliance/AP Photo/M. Euler

የሽታይንማየር እና የማክሮ ማሳሰቢያ

የጀርመን ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑዌል ማክሮ አውሮጳውያን ለጋራ መጻኤ እድላቸው በየሀገሩ ብሔረተኝነትን ለመዋጋት በጋራ መቆም እንደሚገባቸው አሳሰቡ። ለአንደኛው የዓለም ጦርነት ማብቂያ 99 ነኛ ዓመት መታሰቢያ አልዛስ ፈረንሳይ ውስጥ የተሰራ የጋራ የጦርነት ቤተ መዘክር ዛሬ መርቀው ይከፍታሉ ተብለው የሚጠበቁት ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች እንዳሉት በሚቀጥሉት ዓመታት የአውሮጳ ህብረት ተጠራጣሪነትን እና ተቃውሞን ከመስፋፋት ማስቆሙ አስፈላጊ እና በአስቸኳይ መፈፀምም ያለበት ጉዳይ ነው። በመሪዎቹ ተመርቆ የየሚከፈተው ቤተ መዘክር ፣በአንደኛው የዓለም ጦርነት 25ሺህ እንደሚሆኑ የተገመተ የጀርመን እና የፈረንሳይ ወታደሮች ካለቁበት አርትማንስቪለርኮፕፍ ከተሰኘው ተራራ አቅራቢያ ነው የሚገኘው። በሁለቱም ወገኖች በስልታዊነቱ ይፈለግ የነበረውን እና በኋላም «ሰው በላ» የሚል ስም የተሰጠው ተራራ የሚገኝበትን አካባቢ ከ1870 እስከ 1871 በተካሄደው የፈረንሳይ እና የፕሩሽያዎች ጦርነት ወቅት ጀርመን ገንጥላ ወስዳው ነበር። ጀርመን በአንደኛው የዓለም ጦርነት ከተሸነፈች በኋላ ግን ፈረንሳይ አካባቢውን መልሳ ወስዳለች። 

ሃይማኖት ጥሩነህ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ