1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ተቋማት በግብፅ

ማክሰኞ፣ ጥር 28 2005

እኢአ 2011 ግብፅ በሚገኘው የጀርመኑ ፤ ኮንራድ -አደናወር መታሰቢያ ድርጅት የታጠቁ ወታደሮች ኮምፒውተሮችና መዝገቦች ይወስዳሉ፣ በወቅቱ ኃላፊ የነበሩት አንድሪያስ ያኮብስም ለረጅም ሰዓታት በምርመራ ጣቢያ እንዲቆዩ ተደርጎ ነበር።

https://p.dw.com/p/17Xwx
ምስል Getty Images

ምንም እንኳን በወቅቱ የግብፆቹ ትኩረት በ ዮናይትድ እስቴትስ ተቋማት ላይ የነበረ ቢሆንም የጀርመኑም ተቋም ርምጃ ሊወሰድበት ተደርጎ ነበር። ግብፅ የሚገኘው የጀርመኑ ተቋም ፤ ኮንራድ -አደናወር መታሰቢያ ድርጅት ኃላፊ፤ ያኮብስ የተነሳባቸው ክስ ተቋሙ ለግብፅ ባለስልጣናት በሚገባ ሳያሳውቅ በውጭ ሀገራት ገንዘብ ተገልግሏል የሚል ነበር። ጀርመን ይህንን አጥብቃ ተችታለች። የጀርመን የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤቱም ቢሆን በጉዳዩ ተቆጥቷል። ከአመት በፊት በሰጠው መግለጫ የግብፅ ባለስልጣናት በተቋሙ ላይ ያነሱት ወቀሳ መሰረተ ቢስ እና ትርጉም የለሽ ነው ነው ያሉት።

Mursi in Berlin 30.01.2013 Proteste
በጀርመን የግብፁ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ተቃዋሚዎችምስል Getty Images

ምንም እንኳን የያኮብስ ክስ እስካሁን ባይነሳም ዛሬ ሁኔታው የተረጋጋ ይመስላል። የግብፁ ፕሬዚዳንት ሞሀመድ ሙርሲ ያለፈው ሳምንት ጀርመንን በጎበኙነት ወቅት የጀርመኗ መህራይተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የኮንራድ -አደናወር መታሰቢያ ድርጅት ስራ በጀርመን-ግብፅ የባህል ስምምነት ላይ እንደሚያተኩር ይህም ተቋሙ በግብፅ ህጋዊ መብት ይበልጥ እንዲጠናከር ሚና እንደሚጫወት አሳውቀዋል።

ለክሪስትያን ዲሞክራት ፓርቲ ቅርብ የሆነው የጀርመኑ ተቋም ኮንራድ -አደናወር-መታሰቢያ ድርጅት በቅርቡ ስራውን የሚጀምር ይመስላል። በዚህ ሮላንድ ማይርዱስ ያምናሉ። በካይሮ የሌላኛው ለለዘብተኛ ፓርቲ ቅርቡ ተቋም፤ ፍሪደሪሽ-ናውማን-መታሰቢያ ድርጅት ኃላፊ ናቸው።

Andreas Jacobs Büroleiter der Konrad-Adenauer-Stiftung Kairo
አንድሪያስ ያኮብስምስል KAS

« ኮንራድ -አደናወር-መታሰቢያ ድርጅት በቅርቡ መቼ አዲስ የፕሮጀክት ኃላፊ ወደቦታው እንደሚልክ ይመክራል።» የዛን ጊዜ አራት የጀርመን ተቋማት ወደ ካይሮ ተመልሰው ስራ ይጀምራሉ ማለት ነው ። ቀደም ሲል ከተጠቀሱት ሁለት ተቋማት ሌላ ፍሪድሪሽ- ኤበርት- እና ሀንስ-ዛይድል ተቋም ይገኙበታል። ችግሩ ይላሉ ማይርዱስ ፤ የነዚህ ሁሉ ተቋማት አላማ ለግብፃዊያን ግልፅ አለመሆኑ ነው።

ከተቋማቱ በስተ ጀርባ የፖለቲካ የጀርመን የተለያዩ ፓርቲዎች አሉ። ተቋማቱ የተንታኞች ቡድን እንዲሁም የአማካሪ ድርጅቶች ናቸው። አውደ ርዕይና ስብሰባዎች ያዘጋጃሉ፣ ወጣቶችን፣ ፖለቲከኞችንና የመገናኛ ብዙኃን ሰዎችን ያሰለጥናሉ፣ ባለሙያዎችን ወደ ሀገሪቱ ያስገባሉ። እኢአ ከ 1970 ጀምሮ የጀርመን ተቋማት በግብፅ ይገኛሉ። የቀድሞው የ ኮንራድ መታሰቢያ ድርጅት የካይሮ ተወካይ ያኮብስ የተቋሙ አላማ ሀሳቡን የሚገልፅ ዜጋ መፍጠር ነው ይላሉ። ይሁንና የተቋሙ አላማ ባለፉት አስርተ አመታት ሲቀያየር ተስተውሏል።

«ከአብዮቱ በኋላ እጅጉን ወሳኙ ነገር የማህበራዊ የገበያ ኢኮኖሚው ነው። ይህም ማለት የድርጅቶችን እና የማህበረሰባዊ ፍላጎትንን ማመጣጠኑ ላይ ነው። በርካታ የተወናከፉ ነገሮች በሀገሪቷ አሉ። ሙዋለ ንዋይ የሚያፈሱ የሉም፣ ብሔራዊ ያልተጣራ ገቢው ወደ ታች እያሽቆለቆለ ነው። የፓውንዱም ዋጋ ወርዷል።» የጀርመኑ የፖለቲካ ተቋማት ስራ በሀገሪቷ ከተለያዩ ሀጋራት ጋ መወያየት እና መፍትሄ ማግኘት መሆኑን ማይርዱስም ይገልፃሉ።« በአዲስቱ ግብፅ እንዴት አድርገን ቦታ እንደምንይዝ እያሰብን እንገኛለን። ግብፅ ብቻ አይደለም የተቀየረችው እርግጠኛ ነኝ እኛም መቀየር ይኖርብናል።»

ምንም እንኳን እንደ ሌሎቹ ተቋማት ችግር ባይገጥመውም ስራውን ቀንሶ የነበረው የጀርመን ተቋም ፍሪደሪሽ-ናውማን መታሰቢያ ድርጅት መልሶ ስራውን ሊያጠናክር አስቧል። ማይርዱስ እንደሚገልፁት ከእስላማውያን ቡድኖች ጋ የበለጠ ግንኙነት ለመፍጠር ታቅዷል። እስካሁን ተቋሙ የግብፅን ህዝብ ሙሉ ለሙሉ ሊያገኝ አልቻለም ነበር። ነው ያሉት።

ክላውስ ያንስን

ልደት አበበ

ተክሌ የኋላ