1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ጉብኝት

ሐሙስ፣ ጳጉሜን 3 2003

ሰሞኑን ኢትዮጵያ የጎበኙት በጀርመን ፌደራል መንግሥት የሰብአዊ መብት ና የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ተጥሪ ማርኩስ ሎኒንግ በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት አያያዝ ረገድ ይበልጥ መሠራት እንዳለበት አሳስቡ ።

https://p.dw.com/p/Rkei
የጀርመን ፌደራል መንግሥትየሰብአዊ መብትና የሰብአዊ ርዳታ ጉዳይ ተጠሪ፣ምስል picture-alliance/dpa

ሎኒንግ ሃገራቸው ለኢትዮጵያ እርዳታና ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኗን ገልፀው በሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳይም መታየት እንደሚገባውና ትክክለኛ እና ነፃ ምርጫ መካሄድ እንዳለበትም ተናግረዋል ። የዶሎ አዶውን የሶማሊያ የስደተኞች መጠለያ የጎበኙት ባለሥልጣኑ የችግሩን ሰለባዎች እርዳታ እንደሚያሻቸውም አስታውቀዋል ። ከሎኒንግ ጋር ዶሎ አዶ የተጓዘው ጌታቸው ተድላ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ

ሒሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ