1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ርዳታ ለኢትዮጵያ ድርቅ

ዓርብ፣ ጥር 13 2008

የጀርመን መንግሥት ከለግሰው ርዳታ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ለዓለም የምግብ ድርጅት የተወሰነውን ደግሞ ለተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት እንደሚሰጥም ገልጿል። በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ይሰጣል የተባለው ይኽው ርዳታ በተለይ ለነፈሰጡሮችና ለህጻናት የታሰበ መሆኑም ተጠቅሷል ።

https://p.dw.com/p/1HiXM
Dürre – Äthiopien
ምስል European Commission DG ECHO / CC BY-SA 2.0

[No title]

የጀርመን መንግሥት በኢትዮጵያ በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ41.3 ሚሊዮን ዩሮ ርዳታ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ለዶቼቬለ እንዳስታወቀው እርዳታውን በተለይ በድርቅ ለተጎዱት የአፋርና የሶማሊያ ክልል አካባቢዎች ለመስጠት ነው የታሰበው። የጀርመን መንግሥት ከለግሰው እርዳታ ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ለአለም የምግብ ድርጅት የተወሰነውን ደግሞ ለተመ የህፃናት መርጃ ድርጅት እንደሚሰጥም ገልጿል። በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥ ይሰጣል የተባለው ይኽው ርዳታ በተለይ ለነፈሰጡሮችና ለህጻናት የታሰበ መሆኑም ተጠቅሷል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ