1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ፕሬዝደንት ጉብኝትና አድናቆት

ዓርብ፣ ጥር 24 2011

የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማየር ኢትዮጵያ ዉስጥ የተያዘዉ ለዉጥ በሐገሪቱ ዴሞክራሲና ነፃነትን ለማስረፅ መሠረት እንደሚሆን መአስታቁ።ሽታንይማየር ዛሬ ለሰወስተኛ ቀን በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ሲያጠናቅቁ እንዳሉት ኢትዮጵያ የጀመረችዉ ለዉጥ ለሐገሪቱ ታሪካዊ ዕድል ነዉ።

https://p.dw.com/p/3CSu2
Äthiopien Bundespräsident Frank-Walter Steinmeier in Addis Abeba
ምስል DW/A. Steffes

የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ-ቫልተር ሽታይማየር ኢትዮጵያ ዉስጥ የተያዘዉ ለዉጥ በሐገሪቱ ዴሞክራሲና ነፃነትን ለማስረፅ መሠረት እንደሚሆን መአስታቁ።ሽታንይማየር ዛሬ ለሰወስተኛ ቀን በኢትዮጵያ ያደረጉትን ጉብኝት ሲያጠናቅቁ እንዳሉት ኢትዮጵያ የጀመረችዉ ለዉጥ ለሐገሪቱ ታሪካዊ ዕድል ነዉ። ለዉጡ ከኢትዮጵያም፣ከአካባቢዉ፣ከአፍሪቃም አልፎ ለአዉሮጳ ጭምር ተቃሚ ነዉ።                 
«በኢትዮጵያ ባደረጉት የመጨመረሻዉ ቀን ጉብኝቴ ዛሬ፣የተገነዘብቁትን ጠቅለል አድርጌ መናገር እችላለሁ።ባሁኑ ወቅት እዚሕ ኢትዮጵያ ዉስጥ የምናየዉ ለላለቀ ዴሞክራሲና ለተሻለ ነፃነት የሚደረገዉ ለዉጥ ጥልቅ ስሜት አሳድሮብኛል።ይሕ በርግጥ ለዚች ሐገር ታሪካዊ ዕድል ነዉ።እንደሚመስለኝ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን፣ለመላዉ አካባቢዉ፣ለአፍሪቃም ጠቃሚ ነዉ፣ከዚሕም በተጨማሪም ለአዉሮጳም እንደ ጥሩ ዕድል እናየዋለን።»
የጀርመኑ ፕሬዝደንት ካለፈዉ ዕሁድ ጀምሮ ከኢትዮጵያዊቷ አቻቸዉ ከወይዘሮ ሳሕለ-ወርቅ ዘዉዴ፣ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድና ከተለያዩ ወገኖች ጋር ተወያይተዋል።በጀርመን እርዳታ የሚያስተምር የተገባረ ዕድ ትምሕርት ቤትን ጎብኝተዋል። ከአዲስ አበባ ዉጪ ወደ ላሊበላ ተጉዘዉም የላሊበላን ዉቅር አብያተ ክርስቲያናት ጎብኝተዋል።ፕሬዝደንቱ በተለይ ከፕሬዝደንት ሳሕለ-ወርቅና ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር ያደረጉትን እዉነተኛና ከልብ የመነጨ ብለዉታል።  
«በዚሕ የሁለት ቀን ተኩል ቆይታዬ፣ ከለዉጡ አራማጆች ከፕሬዝደንቷና ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የመወያየት ዕድል አጋጥሞኛል።አሁን ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ያደረጉትን  አጠናቅቄ መዉጣኔ ነዉ።ባለፉት ወራት የተደረገዉ ለዉጥና ጉዞ በእዉነተኝነትና ከልብ በመነጨ ስሜት ትኩረት የተሰጠዉ መሆኑን (ተገንዝባሌሁ)።ባለፉት ወራት የተደረገዉ ይሕ ብቻ አይደለም።የፖለቲካ እስረኞች ተለቀዋል፤የቀድሞ ተቃዋሚ (ፖለቲከኞች) በሐገሪቱ ተቋማት እንዲካተቱ ተደርጓልም።»
ፕሬዝደንት ሽታይንማየር በበአዲስ አበባ ቆይታቸዉ ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በተጨማሪ ከአፍሪቃ ሕብረት መሪዎች ጋርም ተዋይተዋል።ፕሬዝደንቱ ወደበርሊን ለመመለስ ዛሬ ቀትር ላይ ከአዲስ አበባ ለመነሳት አቅደዉ ነበር።ይሁንና የጀርመን የዜና ምንጮች እንደዘገቡት ልዩ አዉሮፕላናቸዉ በመበላሸቱ እዚያዉ አዲስ አበባ ሆቴል ለመቆየት ተገድደዋል።ፕሬዝደንቱ ኢትዮጵያን የጎበኙት 55 አባላት ያሉት የፖለቲካ፣የንግድና የባለሙያዎችን ቡድን መርተዉ ነዉ።
 

Berlin, Bundespräsident Frank-Walter Steinmeier geht an Bord der Regierungsmaschine "Theodor Heuss"
ምስል picture-alliance/dpa/B. Pedersen
Bundespräsident Frank-Walter Steinmeier in Äthiopien
ምስል picture-alliance/dpa/B. Pedersen
Äthiopien Afrikanische Union | Bundespräsident Frank-Walter Steinmeier in Addis Abeba
ምስል Deutsche Botschaft in Äthiopien

ነጋሽ መሐመድ 

አዜብ ታደሰ