1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያ ጉብኝት መሰናዶ

ዓርብ፣ ጥር 17 2011

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በመጪው እሁድ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ።  ከፕሬዚዳንቱ  ጋር  የጀርመን የንግድ ማኅበረሰብ ልዑካን አብረዋቸዉ ይጓዛሉ። ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከኢትዮጵያዋ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ እና ከጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

https://p.dw.com/p/3CDHa
DW-Interview mit Frank-Walter Steinmeier
ምስል DW/R. Oberhammer

ኢትዮጵያ ለውጥ በአፍሪቃ ውስጥ የሚንፀባረቅ ነዉ

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የኢትዮጵያን ለውጥ "ከሀገሪቱ ዳር ድንበር አልፎ በአብዛኛው አፍሪቃ ውስጥ ሊንጸባረቅ የሚችል" ሲሉ ይገልጹታል። "ይህ ሲሉ  ግን ለውጡ ፈተና የለውም ማለት እንዳልሆነ ፕሬዚዳንቱ ጠቁመዋል። ፕሬዚዳንቱ ከሲቪክ ማኅበራት ተወካዮች ጋር ለመምከር ቀጠሮ አላቸው ተብሎአል። የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሉ ከአምስት ዓመታት በፊት ኢትዮጵያን ጎብኝተው ነበር። ፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ ከመጓዛቸው በፊት የ«DW» የአማርኛዉ ክፍል ተጠሪ ሉድገር ሻዶምስኪ እና ነጋሽ መሐመድ ቃለ-መጠይቅ አድርገውላቸዋል። ጋዜጠኛ ነጋሽ መሃመድ ከፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ጋር በምን ጉዳይ እንደተነጋገሩ እንዲሁም ስለኢትዮጵያ ያላቸዉን ምልከታ አጠር ባለ ቃለ-ምልልስ ይገልፃቸዋል። ሙሉዉን መሰናዶ የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ።  

 

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ