1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን ጀመሩ

ሰኞ፣ ጥር 20 2011

ትናንት ምሽት ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የገቡት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ጀምረዋል። ፕሬዚደንት ሳህለ ውርቅ ዘውዴ ከጀርመኑ ፕሬዚዳንት ቫልተር ሽታይንማየር ጋር ተወያዩ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል።

https://p.dw.com/p/3CIiF
Deutschland Bundespräsident Steinmeier zu Staatsbesuch in  Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky
Deutschland Bundespräsident Steinmeier zu Staatsbesuch in  Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky

ትናንት ምሽት ኢትዮጵያ መዲና አዲስ አበባ የገቡት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ጀምረዋል። ፕሬዚደንት ሳህለ ውርቅ ዘውዴ ከጀርመኑ ፕሬዚዳንት ቫልተር ሽታይንማየር ጋር ተወያዩ የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል።  የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የጀርመኑን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር በብሔራዊ ቤተ -መንግስት  ዉስጥ ባደረጉት ዉይይት ሃገራቱ በሁለትዮሽ እና ተያየዥ ጉዳዮች ዙሪያ መነጋገራቸዉ ነዉ የተገለፀዉ።  ኢትዮጵያ ከጀርመን ጋር በንግድና ኢንቨስትመንት ዙሪያ  በጋራ ጥቅም በትብብር ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ፍላጎት መኖሩም ተመልክቶአል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት  ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ሃገራቸዉ በንግድ፣በኢንቨስትመንት፣በስልጠናና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብርና በቅርበት የምትሰራ መሆኑን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝታቸዉን መጀመራቸዉ በፊት ጀርመን ላይ በሰጡት ቃለ ምልልስ «ይሕችን ጥልቅ ትርጉም ያላትን ታላቅ አፍሪቃዊት ሐገር በከፍተኛ ፍላጎት እና በታላቅ አክብሮት የምናያት መሆኑን መናገር እንችላለን።አሁን የሚታየዉ (ለዉጥ) በተለይም የለዉጡ አወንታዊ ዉጤቶች፣ ወደ ዴሞክራሲና ምጣኔ ሐብታዊ መረጋጋት የሚደረግ በአካባቢዉም የሚንፀባረቅ ፣ለመላዉ አፍሪቃም በጎ አስተምሕሮ ነዉ።» ብለዉ ነበር።

Äthiopien Addis Abeba Nationalpalast | Bundespräsient Frank-Walter Steinmeier & Sahle-Work Zewde, Präsident
ምስል Deutsche Botschaft in Äthiopien
Deutschland Bundespräsident Steinmeier zu Staatsbesuch in  Äthiopien
ምስል DW/L. Schadomsky

 


አዜብ ታደሰ