1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመኑ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር የኢራቅ ጉብኝት

ረቡዕ፣ የካቲት 11 2001

በሃያ-ሁለት አመት ዉስጥ አንድ የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኢራቅን ሲጎበኝ ሽታይንማየር የመጀመሪያዉ መሆናቸዉ ነዉ

https://p.dw.com/p/GwuN
ሽታይን ማየርና ጀላል ጠላባኒምስል AP

የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ኢራቅን ለመጎብኘት ትናንት ባግዳድ ገብተዋል።በርካታ የኩባንያ ሐላፊዎችንና የንግድ ተቋም ባለቤቶችን ያስከተሉት ሽታይማየር ከትናንት ጀምረዉ ከኢራቅ ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ዉይይት የሁለቱን ሐገሮች ግንኙነት በተለይ በምጣኔ ሐብቱ መስክ ያለዉን ትብብር ለማጠናከር ተስማምተዋል።በሃያ-ሁለት አመት ዉስጥ አንድ የጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኢራቅን ሲጎበኝ ሽታይንማየር የመጀመሪያዉ መሆናቸዉ ነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።