1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶቸ ቬለ ራዲዮ ጣቢያ 60ኛ ዓመት ምሥረታ ልዩ ዝግጅት

ዓርብ፣ ሚያዝያ 25 2005

ሚያዚያ 25 ቀን 2005 ዓም ዓርብ ነዉ ቀኑ። የዶቼ ቬለ ራድዮ ጣቢያ ሥርጭቱን የጀመረበት 60 ኛ ዓመት ዛሬ ነው ፤ የዶይቸ ቬለ የአማርኛው ቋንቋ ክፍል ደግሞ ከሁለት ዓመት በኋላ 50ኛ ዓመቱን ይይዛል።

https://p.dw.com/p/18S7V
Die Deutsche Welle steht 2013 seit 60 Jahren im Dialog mit der Welt. Sendestart war der 3. Mai 1953. Artikelbild Amharisch
ምስል DW


ስለ ዶቼ ቬለ ምን ትዉስታ አላችሁ?! ዶቼ ቬለ የተመሠረተበትን 60ኛ ዓመቱን ሲያከብር፤ ዓለማቀፍ የፕሪስ ነፃነት ቀን የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የተዘጉ ጋዜጦችን እያሰቡ ማክበራቸዉ ኢትዮጵያዉያን የግል ጋዜጠኞች ገለጹ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) በአሸባሪነት ተወንጅላ ለታሠረችዉ ለርእዮት ዓለሙ ያዘጋጀላት ሽልማት ዛሬ በኮስታሪካ የሚሰጥ  ሲሆን ሽልማቱን International women’s  media Foundation እንዲቀበልላት መወከልዋን ቤተሰቦችዋ ተናግረዋል። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ልኮልናል።
በስደት ላይ የሚገኘዉ የተዘጋችዉ የአዲስ ነገር ጋዜጣ፤ ዋና አዘጋጅ  መስፍን ነጋሽ፤ Reporters Without Borders የተሰኘዉ የጋዜጠኞች መብት ተማጋች ድርጅት የጎርጎረሳዉያኑን 2013 ዓ,ም የፕረስ ነጻነት ሽልማት መቀበሉ ዛሬ ይፋ ሆንዋል። ከመስፍን ሌላ ኢትዮጵያ ዉስጥ በአሸባሪነት ወንጀል እያንዳንዳቸዉ 11 ዓመት ተበይኖባቸዉ በምህረት የተለቀቁት ሁለት ስዊድናዉያን ጋዜጠኞች ማርቲን ሽብዩ እና ዮሃን ፔርሸን ይህንኑ  የ Reporters Without Borders ን  ሽልማት አግኝተዋል። ዘገባ አለን።
ዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ በርካታ አድማጮቻችን የተለያዩ አስተያየቶች በየጊዜዉ ለዝግጅት ክፍላችን ይደርሳሉ። 60 ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ  የDC ዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ያሰባሰባሰባቸዉን አስተያየቶችም ይደመጡበታል። የዶቸ ቬለ ራዲዮ ጣቢያ ስድሳኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት በእስራኤል የሚኖሩትን አድማጮቻችንን አስተያየት ወኪላችን ግርማዉ አሻግሬ አሰባስቦልናል።  የዕለቱ የዜና መጽሔት በፕረስ ነጻነት እና በዶቼ ቬለ የምሥረታ በዓል ላይ በማተኮሩ  ባልደረቦቻችንን ፣ ተክሌ የኋላን እና  ነጋሽ መሐመድን ስለዶቼ ቬለ ራዲዮ ጣቢያ ያላቸዉን አስተያየት አስደምጠዉናል።  
የዶቼ ቬለን 60 ኛ ዓመት የምሥረታ ዕለት ምክንያት በማድረግ ከመካከለኛዉ ምሥራቅ፤ ከአፍሪቃ፤ ከአዉሮጳ እና ከሌሎችም የዓለም ክፍሎች የተለያዩ አስተያየቶች በተለያየ መንገድ ደርሶናል። የስርጭት ጊዜአችን ዉስን በመሆኑ ሁሉንም ለማቅረብ ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን። ለሰጣችሁት አስተያየት በጣም እናመሰግናለን።  ከሁለት ዓመት በኋላ የአማርኛዉ ክፍል የተመሠረተበትን 50 ኛ ዓመት ያከብራል። እስከዚያ እና በዚያ ጊዜ  አስተያየት መስጠታችሁን እና ዝግጅታችንን መከታተላችሁን እንደምትቀጥሉ ተስፋ እናደርጋለን ። 50ኛ ዓመቱን በዓል አብረን ለማክበር ያብቃን፤ በያላችሁበት መልካሙን ሁሉ እንመኝላችኋለን። ሙሉዉን ዝግጅት ከታች ያለዉን የድምፅ ማሳያ ምልክት በመጫን ያድምጡ!    
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

gemischte Bilder aus Redaktionskonferenzen und Redaktionsalltag etc. zum Thema: Bildergalerie 60 Jahre DW Radiosendungen Dari Pashto und Urdu *** eingestellt im März 2013, Copyright: DW
ምስል DW
gemischte Bilder aus Redaktionskonferenzen und Redaktionsalltag etc. zum Thema: Bildergalerie 60 Jahre DW Radiosendungen Dari Pashto und Urdu *** eingestellt im März 2013, Copyright: DW
ምስል DW
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ