1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶቸ ቬለ መታፈን

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 4 2003

አቶ በረከት ስምዖን «የሞገድ አፈና አልተደረገም» የሚል ቃል ለሮይተርስ የዜና አገልግሎት ድርጅት ከመስጠታቸውም፤ የዶጨ ቨለ ራዲዮ ሥርጭትን 1 ከመቶ ኢትዮጵያውያን ናቸው የሚያዳምጡት ብለዋል

https://p.dw.com/p/RHQa
ምስል AP

ዶቸ ቨለ፣ የጀርመን ድምፅ ራዲዮ፣ ከአንድ ሳምንት ገደማ ወዲህ አንስቶ የማሠራጫ ሞገዶቹ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውክም ሆነ የሚያፍን ድምፅ እንዳገጠማቸው በመጥቀስ የራዲዮ ጣቢያው ባለሥልጣናት፣ ሥርጭቱ፤ ከእውካ ነጻ ስለሚሆንበት ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግሥት ይተባበር ዘንድ መጠየቃቸው የሚታወስ ነው። የኢትዮያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ስምዖን «የሞገድ አፈና አልተደረገም» የሚል ቃል ለሮይተርስ የዜና አገልግሎት ድርጅት ከመስጠታቸውም፤ የዶጨ ቨለ ራዲዮ ሥርጭትን 1 ከመቶ ኢትዮጵያውያን ናቸው የሚያዳምጡት ብለዋል። ይህን አባባላቸውን ያረጋገጠላቸው መረጃ አቅራቢውም ገለልተኛ ጥናት አካሄዷል ያሉት Electoral Reform International Services የተሰኘው ነው። ይህ አጥኚ ድርጅት ማን ነው፣ የማን ነው? የለንደኑ ዘጋቢአችን ድልነሣ ጌታነህ ክትትል አድርጎ ነበር።

ድልነሣ ጌታነህ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ