1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድንጋይ ንጉሱ እና ጥንታዊዉ የመገበያያ ገንዘብ

ሰኞ፣ መጋቢት 17 1999

የኢትዮጽያ የገንዘብ አመጣጥና ታሪክ በአጠቃላይ የየዘመኑን ስርአት እና ህግን የተከተለ ቢሆንም የራሱ የሆነ ባህሪም ነበረዉ ማለት ይቻላል። በዘመነ አክሱም ወደ ሃያ አምስት የሚሆኑ ነገሥታት የራሳቸዉን ገንዘብ አሳትመዉ የልዉዉጥ ስርአቱ የረቀቀ እና ከፍተኛ ደረጃ የደረሰ እንደ ነበር ጹሁፎች ይገልጻሉ

https://p.dw.com/p/E0mO
ከአክሱም ዉድቀት በኳላ የኢትዮጽያ ስልጣኔ ያልጠፋ ቢሆንም እስከ አስራ ዘጠነኛዉ ምዕተ አመት መጨረሻ ድረስ አንድም ገንዘብ ያሳተመ ንጉስ እንዳልነበር ጥናቶች ያስራዳሉ። በኢትዮጽያ የጨዉ ገንዘብ ማለት አሞሌ ከሺህ አመት በላይ በግብይት ሂደት ዉስጥ የገንዘብ ሚና ሲጫወት እንደነበር መናገር ይቻላል። በኢትዮጽያ አሞሌ ጨዉ የማርትሪዛ ብር የኢንግሊዝ ሽልንግ ከዚያም አልፎ ጥይት የመገበያያ ገንዘብ እንደነበር ይታወሳል። አንጋፋዉ ጋዜጠኛ እና ደራሲ ማሞ ዉድነህ የኢትዮጽያን የጥንት የመገበያያ ዘዴ ያወጉናል።