የዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ እና የስዊድን ሕግ ባለሙያዎች ጥያቄ
ረቡዕ፣ መስከረም 14 2007ማስታወቂያ
የሕግ ባለሙያዎቹ ጥያቄ በዋነኝነት ያተኮረው በኤርትራ በእስር የሚገኘው ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅ ጉዳይ ላይ ነው። ዓቃቤ ሕግ ጉዳዩን ማጣጣሉን ድንበር የማይገድበው የጋዜጠኞች ድርጅት አሳፋሪ ብሎታል። ጋዜጠኛው ዳዊት ይፈታ ዘንድ ከሕግ ባለሙያዎቹ ጎን ድምፃቸውን የሚያሰሙ ወገኖችም የዳዊት ጉዳይ በአውሮጳ ሀገራትም ትኩረት ያገኝ ዘንድ የዳዊትን ስራ በተለያዩ ቋንቋዎች አስተርጉመው ለማውጣት እየሰሩ መሆናቸውን የስቶክሆልሙ ዘጋቢያችን ቴድሮስ ምህረቱ ገልጾልናል።
ቴድሮስ ምሕረቱ
አርያም ተክሌ