የዳኛ ዉሳኔና የትራምፕ ይግባኝ በአሜሪካ
ማክሰኞ፣ ጥር 30 2009ማስታወቂያ
ሳንፍራንሲስኮ ግዛት በሚገኘዉ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ዉሳኔዉን ለማስቀልበስ ያቀረበዉ አቤቱታ በድጋሚ በፌደራሉ የይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዉድቅ መደረጉ በሀገሪቱ ጉዳዩን አነጋጋሪ አድርጎታል። ጉዳዩ ወደ ሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተወሰደ ሲሆን ዛሬ ለአንድ ሰዓት የሚዘልቅ ክርክር እንደሚካሄድበት ይጠበቃል። የፕሬዝደንቱ ዉሳኔ ከሀገሪቱ ሕግ እንደሚፃረር የሚገልፁ ወገኖች ፍርድ ቤት የሀገሪቱን መሪ ዉሳኔ መጣል የቻለዉ የሕግ የበላይነት ያለባት በመሆኗ እንደሆነ ይናገራሉ። ከዋሽንግተን ዲሲ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝሩን ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ